አሸባሪው ህወሓት በውርጌሳ 13 ንጹሃንን በጋዝ አርከፍክፎ አቃጠለ

(ኢ ፕ ድ) – አሸባሪው ህወሓት በውርጌሳ ከተማ 13 ንጹሃንን በአንድ ቤት ውስጥ በጋዝ አርከፍክፎ ማቃጠሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል።-
ህወሓት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሁሉ ንጹሃንን በጅምላ እየገደለ ሲሆን በውርጌሳ 13 የአማራ ተወላጆችን በአንድ ቤት ውስጥ ጋዝ አርከፍክፎ እንዳቃጠላቸው የዓይን እማኞች ገልጸዋል::
የሽብር ቡድኑ በውጫሌ ከተማ ባደረገው የከባድ መሳሪያ ድብደባ ከ30 በላይ ንጹሃን መገደላቸውን የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ከትላንት በስቲያ በሰጡት መግለጫ መናገራቸው የሚታወስ ነው።