የሕወሓት አዲስ ጥቃት በአፋር

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከጥቅምት 1 ቀን፤ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በአፋር ክልል ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተገለጠ። የአፋር ክልል ባለስልጣናት ለዶይቼ ቬለ እንዳረጋገጡት በአፋር ክልል ዞን አራት፤ እዋ ወረዳ፤ ፈንቲረሱ በምትባል ስፋራ ላይ ባነጣጠረው የከባድ ጦር መሣሪያ ጥቃት የንጹሃን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ  ተቀጥፏል።…