የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ወደ ምስራቅ ወለጋ እየተሻገሩ ነው። – ኦነግ ሸኔ

አዲስ ስታንዳርድ ባወጣው ዘገባ ኦነግ ሸኔን ጠቅሶ እንደፃፈው የታጣቂ ቡድኑ በተደጋጋሚ እንዳስጠነቀቀው በኦሮሞ እና በአማራ ሰላማዊ ዜጎች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ወደ ምስራቅ ወለጋ እየተሻገሩ ነው። በዚህ ሳምንት ከተገደሉት 25 ንፁሃን የኦሮሞ ሰላማዊ ዜጎች 17 ቱ የአንድ ቤተሰብ ናቸው። ሲል ጠቁሟል።

አዲስ ስታንዳርድ አናገርኳቸው ያላቸው የኦሮሞ ማሕበረሰብ አባላት በአማራ ሚሊሻ ጥቃት ተሰንዝሮብናል ብለዋል።

የመብቶች ኮሚሽን በምስራቅ ወለጋ በሰላማዊ ዜጎች የፀጥታ ሁኔታ ላይ ስጋቱን ከገለጸ ከሳምንታት በኋላ በኪራሙ ወረዳ የጋራ ብጥብጥ ተከሰተ ያለው አዲስ ስታንዳርድ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ከአማራም ሆነ ከኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ዘገባዎችን አግኝቷል። ከሁለቱም ማህበረሰቦች አባላት እና ከማህበረሰቡ መሪ የተቀበሉት ምስክርነት ጥቅምት 10 እሁድ የብዙ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ማድረጉን ያሳያል። ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ ይፋ ያደረጉት ግጭቱ እኩለ ቀን ጀምሮ እስከ ቀኑ ድረስ መግባቱን ነው።

ከዚሁ ጋር የተያያዘው መርጃ እንደሚጠቁመው የገባው የጸጥታ ኀይል እንዲወጣ ተደርጎ በኦነግ ሸኔ ጥቃት ተፈጽሟል ሲሉ ከምስራቅ ወለጋ ሸሽተው ያመለጡ ዜጎች መናገራቸው ታውቋል ።

የገባው የጸጥታ ኀይል እንዲወጣ ተደርጎ በኦነግ ሸኔ ጥቃት ተፈጽሟል – ከምስራቅ ወለጋ ሸሽተው ያመለጡ ዜጎችበምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ቀበሌ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአማራዎች ላይ በከፈቱት ጥቃት የንጹሃን ህይወት ማለፉን እና ንብረት መውደሙን የጥቃቱ ሰለባ ቤተሰቦች ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው በተደጋጋሚ እየደረሰ ባለው ጥቃት ሸሽተው እንደመጡ የገለጹት የተጠቂ ቤተሰቦች ከትናንት እኩለ ቀን ጀምሮ ደግሞ በቤተሰቦቻቸው ላይ የሸኔ ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸማቸውን ነግረውናል፡፡
ከዚህ በፊት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በዞኑ ውስጥ በሚኖሩ አማራዎች ላይ በከፈቱት ጥቃት የንጹሃን ዜጎች ሕይወት ማለፉንና በርካታ ንብረት መውደሙን አስታውሰው ትናንት ደግሞ ከዚህ በፊት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአንድ ላይ በሚኖሩባት የሀሮ ቀበሌ በተከፈተ ጥቃት ንብረት መውደሙን እና የንጹን ህይወት ማለፉን ነው የገለጹልን፡፡
As the OLA has warned several times, Amhara regional militia are crossing into East Walaga in order to spark conflict between Oromo and Amhara civilians. This week, out of the 25 innocent Oromo civilians killed, 17 belonged to one family.

ተጨማሪ ዘገባውን ከዚህ ያገኛሉ https://addisstandard.com/news-analysis-weeks-after-rights-commission-expressed-concerns-over-the-security-situation-of-civilians-in-east-wollega-communal-breaks-out-in-kiramu-woreda/