በድሬደዋ የደንጊ በሽታ ወረርሽኝ ተከሰተ

በድሬደዋ ከተማ የደንጊ በሽታ ወረርሽኝ መከሰቱን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ለምለም በዛብህ እንዳሉት ለ87 ናሙናዎች ምርመራ ተደርጎ አራት ሰዎች በደንጊ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከመስከረም እስከ ኅዳር ባሉት ወራት በድሬደዋ ቺኩንጉንያ፣ ደንጊ እና ወባ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ ይከሰታሉ…