የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ባለስልጣናት ከቤተሰቦቻቸውና ከጠበቆቻቸው ተሰውረዋል ተባለ

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ በተፈጠረው ሁከት የተጠረጠሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ባለስልጣናት የታሰሩበትን ቦታ እንደማያዉቁ ቤተሰቦቻቸው ገለፁ። በእስር ላይ የሚገኙት የኦነግ ፖለቲከኛ ቤተሰቦች እንደሚሉት እስረኞቹ ላለፉት ሦስት ወራት ታስረው ከቆዩበት ገላን ፖሊስ ጣቢያ ከትናንት በስቲያ አመሻሽ ጀምሮ ወዴት እንደተወሰዱ እስካሁን የሚያውቁት ነገር የለም። አንድ የግንባሩ ባለስልጣን እና የእስረኞቹ የህግ ጠበቃ እስከ ማክሰኞ መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሲከታተሉ መቆየታቸዉን እና አሁን ግን የት እንደደረሱ እንደማያዉቁ ፤ ግን ከእስረኞቹ መካከል በብዛት በፍርድ ቤት ነጻ መባላቸዉን ገልፀዋል። DW