ብ/ ጀነራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ የአማራ ክልል አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡

Image may contain: 2 people, people sitting

ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ተሾሙ።

በሶስት ፓርቲዎች ጥምረት የተመሰረተውን የኦሮሞ አንድነት ነፃነት ግንባር ሲመሩ የቆዩት ብርጋዴር ጀነራሉ፥ መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ በቅርቡ ወደ ሀገር ውሰጥ መግባታቸው የሚታወስ ነው።

ኤፍቢሲ እንደዘገበው ከዚህ ባለፈ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በርዕሰ መስተዳድሩ የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ታውቋል።

Image may contain: 1 person

ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ሹመቱ የተሰጣቸው በጸጥታው ዘርፍ ያላቸውን የረዥም ጊዜ ልምድና ብቃትን ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን ከምንጮቻችን ባገኘነው መረጃ አረጋግጠናል፡፡

ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡