ኢትዮጵያ ከጥገኝነትና ከተመፅዋችነት ትላቀቅ!

ኢትዮጵያ ከጥገኝነትና ከተመፅዋችነት ትላቀቅ!
May be a drawing of mapኢትዮጵያ ከማንኛውም ዓይነት የውጭ ተፅዕኖ መገላገል የምትችለው፣ ኢትዮጵያዊያን አገራቸው ሰላም እንድትሆን ተመሳሳይ አቋም ሲኖራቸው ነው፡፡ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ የሚገቡትም ሆነ በተለያዩ መንገዶች የሚያስፈራሩት፣ ሰላምና መረጋጋት ጠፍቶ ዕልቂትና ውድመት በመበርከቱ ነው፡፡
ለኢትዮጵያ የሚበጃት የሕዝቧ ሰላምና አንድነት ነው፡፡ ሰላምና አንድነት በመፈላለግ፣ በመከባበር፣ በመፈቃቀርና በመተሳሰብ ላይ እንዲመሠረት ከአውዳሚ ድርጊቶች መታቀብ ያስፈልጋል፡፡ ሰላምና መረጋጋት በሌለበት ዕድገት አይታሰብም፡፡
የሰላም መንገድ ተዘግቶ ጦርነቱ አድማሱን የሚያሰፋ ከሆነ፣ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት እየተጠናከረ በራስ መወሰን ያቅታል፡፡ ኢኮኖሚው ደቆ ረሃብና እርዛት ይከተላሉ፡፡ እንኳንስ የማዕቀብ ማስፈራሪያ እየመጣ ይቅርና እንዲሁም እንደ ነገሩ የሆነው ኢኮኖሚ፣ ብዙኃኑን ሕዝብ መታደግ አቅቶት አስመራሪው ድህነት በስፋት ተንሰራፍቷል፡፡ በጦርነት ጊዜ ኢኮኖሚው እንዴት ይመራ? የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር ምን ይደረግ? ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ የትኞቹ ዘርፎች ላይ በስፋት ይሠራ? ለተቸገሩ ወገኖች መደረግ ካለበት ዕርዳታ በተጨማሪ ለዘለቄታዊ መፍትሔው ምን ይደረግ? የሚሉና ሌሎች መሠረታዊ ጉዳዮች ትኩረት ይፈልጋሉ፡፡
ማንም እየተነሳ ማዕቀብ ሲጥል ወይም የሚያዳክም ድርጊት ሲፈጽም ሸብረክ ማለት የማይቻለው፣ ኢትዮጵያዊያን አገራቸው የሥራ ምድር እንድትሆን ቁርጠኝነት ሲኖራቸው ነው፡፡ ሰላምና መረጋጋት የሚሰፍነው አገራዊ ጥንካሬ ሲኖር ነው፡፡ ይህ ጥንካሬ ደግሞ ከጥገኝነትና ከተመፅዋችነት ያላቅቃል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: http://bit.ly/3o26WiM