የኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ባለውለታ የሆነው የአሰልጣኝ ስዩም አባተ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ።

የቀብር ስነስርዓት ቪዲዮዎች ከታች ይገኛሉ።

አሰልጣኝ ስዩም አባተ ከአባቱ ከአቶ አባተ በቀለና እና ከእናቱ ከወ/ሮ ማሚቴ ገ/ስላሴ በሚያዝያ ወር1943ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ፍልውሀ በሚባለው ሠፈር ነበር የተወለደው፡፡

ዕድሜው ለትምህርት እንደ ደረሰም ከ1ኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በበየነ መርዕድ ት/ቤትና የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን በአባ ሀና ጅማ ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡

ወደ ስራ ዓለምም በገባ ጊዜ በብሔራዊ ትምባሆ ሞኖፖል፣በሕዝብ ማመላለሻ እንዲሁም በቡና ኮርፖሬሽን አገልግልሏል፡፡

በስፖርቱም ዓለም በተጫዋችነት ዘመኑ

1ኛ. ለቅ.ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን ከሕፃናት አስከ ዋናው ቡድን ድረስ
2ኛ. ለትግል ፍሬ
3ኛ. ለሸዋ መርጥ
4ኛ. ለመኢሰማ ምርጥ ቡድን
5ኛ.እንዲሁም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለረጂም ዓመታት ተጫውቶ አሳልፏል፡፡

የአሠልጣኝነት ዘመኑ ያሰለጠናቸው ክለባት ፡- ለቆርኪና ጣሳ ቡድን፣ለብሔራዊ ትምባሆ ሞኖፖል፣ ለሕዝብ ማመላለሻ፣ ለኢትዮጵያ ቡና፣ ለመድህን ድርጅት፣ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለሰሚት እግር ኳስ ቡድን ፣ለኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለብርሀንና ሠላም ሲሆኑ
በሀገር ደረጃ፡- የኢትዮጵያ ታዳጊና ወጣት ብሔራዊ ቡድን፣ የኦሊምፒክ ቡድን፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ዋናውን ብሔራዊ ቡድን አሠልጥኗል፡፡
በዚህም ሙያዊ ስራው ስም ያላቸውን ታላላቅ ተጫዋቾች አፍርቷል፡፡

በቴክኒካል ዳይሬክተርነት

የኢትዮጵያ ቡናን፣ የብሔራዊ ትምባሆ ሞኖፖልን፣የቄራ አንበሳ ቡድንን እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን በማማከር ሙያዊ ሕይወቱ እስከለፈበት ጊዜ ድረስ ደከመኝ ሠለቸኝሳይል ለስፖርቱ እና ለሀገሩ አገልግለዋል፡፡

ስዩሜ ከ1964 ዓ.ም ከባለቤቱ ከወ/ሮ ዙርያሽወርቅ አበራጋር ትዳር የመሠረተ ሲሆን ሶስት ወንድ ልጆችና ሶስት ሴት ልጆችን በአጠቃላይም ስድስት ልጆችን በአርባ ስድስት ዓመት የትዳር ቆይታቸው ውስጥ አፍርተዋል፡፡

የክለባችን ስራ አመራር ቦርድ፣ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ፅ/ቤት ስራተኞች እና በመላው ደጋፊያችን ስም የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE