ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጥያቄ ያቀረቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይቅርታ ጠየቁ

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጥያቄ ያቀረቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይቅርታ ጠየቁ

ቤተመንግስት በመሄድ ለጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጥያቄ ያቀረቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመንግስትና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ ጠየቁ፡፡

የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ ህዝቡን ለመካስ ይበልጥ ጠንክረው እንደሚሰሩም አስታውቀዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ ይቅርታ የጠየቁት ከመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመኮንኖች ክበብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

በውይቱ የመከላከያ አባላቱ የሄዱበት አካሄድ የተቋሙን አሰራር የጠበቀ እንዳልሆነ ከመግባባት ላይ መድረሳቸውም ታውቋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊቱን ጥያቄዎች በቀጣይ ሊፈቱ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE