ታጥረው የቆዩ መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ ከማስገባት ውጭ ለማንም ተላልፈው አለመሰጣተቸው ተገለጸ
ለረዥም ጊዜ ታጥረው የቆዩ መሬቶችን ወደ ባንክ ከማስገባት ውጭ ለማንም ተላልፈው አለመሰጠታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት ማናጅመንት ቢሮ ገለጸ፡፡
በቢሮው የሊዝ ክትትልና አፈፃፀም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በየነ ላምቢሶ እንደተናገሩት በባንኩ ያሉ መሬቶች ወደፊት የከተማውን ፕላን ባገናዘበ መልኩ የሚተላለፉ ይሆናል ብለዋል᎓᎓
ከአልሚዎች የተነጠቁ መሬቶች ለሌሎች እየተሰጡ ነው በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሃሰት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የተነጠቁ መሬቶች ባለሃብቶች አስከያዙበት ጊዜ ያለው የሊዝ ዋጋ አንዲከፍሉ ይደረጋል ሲሉ ገልፀዋል᎓᎓
በቅርቡ በሁሉም ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ ወረራ መኖርያ ቤት የሰሩ በሙሉ የማፈራረስ ተግባር ይከናወናል ብለዋል᎓᎓
የከተማዋ መሬት ማስተር ፕላኑ በሚፈቅደው መሰረት ብቻ የሚተላለፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE