ኢትዮጵያ 19 በመቶ ባለድርሻ የሆነችበት በሶማሌላንድ የሚገኘው የበርበራ ወደብ ግንባታ ተጀመረ፡፡

ኢትዮጵያ ባለድርሻ የሆነችበት የበርበራ ወደብ ግንባታ ተጀመረ

ኢትዮጵያ 19 በመቶ ባለድርሻ የሆነችበት በሶማሌላንድ የሚገኘው የበርበራ ወደብ ግንባታ ተጀመረ፡፡

የሶማሌላንድ አስተዳደር ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች እና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች በትላንትናው ዕለት የግንባታ ማስጀመር ስነ-ስርዓቱ ላይ ተካፍለዋል፡፡

ዲፒ ወርልድ የተባለው የኤምሬትስ ኩባንያ በ420 ሚሊዮን ዶላር የበርበራ ወደብን ግንባታ ለማካሄድ ውል ገብቶ ስራውን ጀምሯል፡፡

በስምምነቱ መሰረት በወደቡ ግንባታ ዲፒ ወርልድ 51 በመቶ፣ የሶማሌላንድ አስተዳደር 30 በመቶ እና የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ 19 በመቶ ድርሻ ይዘዋል ተብሏል፡፡

ግንባታ ከተጠናቀቀ በኋላ ስምምነቱ ለ30 ዓመት የሚቆይ መሆኑንም ተመልክቷል፡፡

የሶማሌላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ በስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የበርበራ ወደብ ግንባታ እውን መሆን የሶማሌላንድ ኢኮኖሚን ከማነቃቃት ባሻገር ለቀጠናው የንግድና ኢኮኖሚ ትስስር ፋይዳው የጎላ ነው፡፡

ምንጭ፡-ሶማሌላንድ ሰን


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE