በኢትዮጵያ የአጎዋ ዕድል ላይ የተነሳው የአሜሪካ ጥያቄ ማንን ይጫናል?

ኢትዮጵያ ለሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፍትሔ ካልተበጀ በአጎዋ ያለ ቀረጥ ምርቶቿን ለአሜሪካ ገበያ የማቅረብ ዕድሏን ልታጣ እንደምትችል የአሜሪካ ባለሥልጣን አስጠንቅቀዋል። አሜሪካ ይኸን እርምጃ ከወሰደች ባለሙያዎች እንደሚሉት ምርቶቻቸውን ከሚልኩ ኩባንያዎች በተጨማሪ በአገሪቱ የሥራ ፈጠራና ድህነት ቅነሳ መርሐ ግብሮች ላይ ጫና ይኖረዋል…