በርከት ያሉ ስልጠናዎችንና ሴሚናሮች እንኳን ቢደረጉ አሁን ያለውን አይነት የህዝቡን አንድነት ማምጣት ይከብዳል – ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

May be an image of 2 people, people standing and indoorሙሀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አሁን ስለተፈጠረው አገራዊ አንደነትና ኢትዮጵያዊነት በባህርዳር….‼

👉 በርከት ያሉ ስልጠናዎችንና ሴሚናሮች እንኳን ቢደረጉ አሁን ያለውን አይነት የህዝቡን አንድነት ማምጣት ይከብዳል፤

👉 አዲሱ ትውልድ በየስልጠና ጣቢያዎች የኢትዮጵያ ስም ሲነሳ በጥልቅ ሀገራዊ ስሜት ሲያነባ ታይቷል፤

👉 ይህን ስናይ ይህን አይነት አንድነትና ስሜት በምን እናገኘዋለን እንላለን፤

👉 አሁን ግን አሸባሪ ቡድኑ በፈጸመው ክፋት አንድነቱ መጥቷል፤ ህዝብ በህብረት ቆሟል፤

👉 ሰዎቹ ለእርግማን እንጂ ለምርቃት ስለሚያስቸግሩ እንጂ አንድነታችንን አምጥተውታል፤

👉 ጥቅማቸውን ቀድመን አውቀነው ቢሆን ኖሮ ምናለ መውጣታቸው ካልቀረ ቀደም ብለው ቢወጡ እንላለን፤

👉 ጥቅሙን እንዲህ መሆኑን ብናውቅ ኖሮ፡ ቀድመን ብናውቀው ኖሮ ቀደም ብለን እናስወጣቸውም ነበር፤

👉 ይህንን አንድነታችንን ለመጠቀም በቀጣይነት ሁለት ስራዎች ያስፈልጉናል፤

👉 አንድም ከሰይጣን የመጨረሻዎቹ የሆኑት ሰዎች ዳግም በኢትዮጵያ መሬት ላይ እንዳይበቅሉ ማድረግ ያስፈልጋል፤

👉 ይልቁንም የህጻናት ማስፈራሪያ ሆነውብእንደ ጭራቅ እንዲታወሱና ቀጣዩ ትውልድ እንደነሱ አይነት ክፉ እንዳያይ ልናደርግ ይገባል። የኢትዮጵያ ምድር እንደነዚህ አይነት ጭራቆች እንዳያፈራ ማድረግ ይገባል፤

👉 በሌላ በኩልም የአንዱን ክልል ባለሃብት ወደሌላው ሲሄድ ልዩ እንክብካቤ በማድረግ ይበልጥ ወንድማማችነቱን ማጠናከር ይገባል፤

Source – EPA