ወሎ የተፈናቃዮች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ሲሆን አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት ዞር ብለው ተፈናቃዩን አላዩትም

May be an image of 14 people and people sitting“… የተፈናቃዮች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ በመሆኑና ደሴ ከተማ ከዚህ በኋላ ተፈናቃዮችን መቀበል ስለማትችል ወደ ኮምቦልቻ እየላክናቸው ነው ” – የደሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሰኢድ የሱፍ

ደሴ በጦርነት ምክንያት ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎች እያስተናገደች መሆኑ ይታወቃል፤ የተፈናቃዮች ቁጥር ግን ከተማዋ ከምታስተናግደው አቅም በላይ በመሆኑ ወደ ኮምቦልቻ ከተማ እየተላኩ ነዉ።

በአሁን ሰዓት ከሰሜን ወሎ ዞን በርካታ አካባቢዎች በጦርነት የተፈናቀሉ ዜጎች በደሴ እና ኮምቦልቻ ተጠልለዋል።

የደሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሲኢድ የሱፍ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ በሰጡት ቃል ፥ በደሴ ከተማ በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ዜጎች ቁጥር 275 ሺህ መድረሱን አመልክተዋል።

May be an image of 10 people, people standing, crowd and roadምክትል ከንቲባው እንዳሉት የተፈናቃዮች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ በመሆኑና ደሴ ከተማ ከዚህ በኋላ ተፈናቃዮችን መቀበል ስለማትችል ወደ ኮምቦልቻ እየተላኩ ነው።

ከተፈናቃይ ዜጎች ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣት አንጻር ደሴ ከተማ የቦታ እጥረት አጋጥሟልም ተብሏል።

ከሰሜን ወሎ የተፈናቀሉ 275 ሺ ዜጎች በመንግስት የተመዘገቡት ብቻ ናቸው ያሉት አቶ ሰኢድ፣ ከቤተሰብ ጋር የተጠለሉት ቁጥር በዉል እንደማይታወቅና ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ጠቁመዋል።

ከተፈናቃይ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የእርዳታ ተደራሽነት ችግር መኖሩን የተናገሩት ምክትል ከንቲባዉ፣ እስካሁን ዩኒቨርሲቲዎች ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ግን ወደ አካባቢው እንዳልሄዱም አረጋግጠዉልናል።

Credit : Ethio FM 107.8