ዉይይት፤ የ2013 ዕዉነትና የ2014 ተስፋ

2013፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ የጦርነት፣ የግጭት፣ የበሽታና  የተፈጥሮ መቅሰፍቶች ጥፋትና ዉድመት ከተመዘገቡባቸዉ ዘመናት አንዱ መሆኑ ብዙ አያጠያይቅም።የጎሳዎች ግጭት፣የፖለቲካ ሽኩቻና የስልጣን ሽሚያ በተለይ ሰሜን፣ሰሜን-ምዕራብና ምዕራብ ኢትዮጵያ ብዙ ሺዎችን የገደለ፣ሚሊዮኖችን ያፈናቀለና ብዙ ሚሊዮኖችን ለረሐብ ያጋለጠ ጦርነትና ጥቃት አስከትሏል…