በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ ወታደሮችን ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ ለመመልከት ችያለሁ።

በኤልያስ መሰረት

ወደ ቤተ- መንግስት እና ebc አካባቢ ከ Elias Gebreselassie ጋር ተንቀሳቅሰን ነበር። ተዘግቶ የነበረው የቤተ- መንግስት መንገድ ከተከፈተ በሁዋላ በእዛ በኩል አልፈን ወታደሮች ወደ ebc አመሩ ሲባል እዛ ብንሄድም ግቢው በፌደራል ፖሊስ ተሞልቶ ነበር።

ከታች የሚታዩት የወታደር ጫኝ መኪናዎች ሸራተን ፊት ለፊት ቆመው ነበር። ወታደሮችን ላናግር ብሞክርም ፈቃደኛ አልነበሩም። በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ ወታደሮችን ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ ለመመልከት ችያለሁ።

ምክንያቱ እስካሁን በ100 ፐርሰንት እርግጠኝነት ባይታወቅም ከጦላይ የመጡ መደበኛ የመከላከያ አባላት በደሞዝ ምክንያት አምፀው/ቅሬታ አሰምተው ነው ተብሏል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE