ግድቡ በቀጣይ ወራት በሁለት ተርባይኖች እስከ 750 ሜጋዋት ኃይል ያመነጫል ተባለ

ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ 13 ተርባይኖች መካከል ሁለቱ ተርባይኖች በሚቀጥለው ዓመት የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምሩ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ለቢቢሲ ገለጹ። “ኃይል ማመንጨት የምንጀምረው ከሁለቱ ተርባይኖች ነው። ይሄ ኧርሊ ጀነሬሽን [የመጀመሪያ ደረጃ የኃይል ማመንጨት] ነው። ሁለቱ ተርባይኖች የሚያመጩት ኃይል እስከ 750 ሜጋዋት ይደርሳል” ሲሉ…