የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን በሱዳን ያሉ ስደተኞች ቁጥር ቢቀንስም ስደተኞቹ የት እንደገቡ እንደማያውቅ ገለጸ

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) በሱዳን በሚገኙ ካምፖች ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ቢቀንስም እነዚህ ስደተኞች የት እንዳሉ ግን እንደማያውቅ ገለጸ። ድርጅቱ ይህን ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን ለስደተኞች የሚሰጥ መታወቂያን የያዙ ግለሰቦች ከህወሓት ወገን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው ማለቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ነው።…