የምሥራቅ ወለጋው ግድያና የኦሮምያ ክልል መንግሥት አስተያየት

ትኩረቱ ሁሉ ሰሜን ኢትዮጵያ ላይ በሆነበት ሰዓት በምስራቅ ወለጋ ከ200 በላይ ንጹሃን በታጣቂዎች መገደላቸውን የገለጹ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪክ ማህበራት መንግሥት በመሰል አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ታጣቂዎች ከሳምንት በፊት በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉት ዜጎች ከ 231 በላይ መሆናቸውን የጠቀሰው እናት ፓርቲ ለምሳሌ ሴቶች…