የኦነግ ሸኔ ጦር የፊንጫ ስኳር ፋብሪካንና አከባቢውን ተቆጣጥሬለሁ ቢልም ከነፃ ምንጭ አልተረጋገጠም። በወለጋ እና በጉጂ አከባቢዎች የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች መቋረጣቸው ይታወቃል። በርካታ ንፁሃን በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገዳላቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ እየተፈናቀሉ መሆኑ ታውቋል ። የኦነግ ሽኔ አለማቀፍ ቃል አቀባይ በለቀቀው መግለጫና ከታች በሚታዩት ቪዲዮዎች ላይ እንደተገለፀው የኦነግሸኔ ጦር የፊንጫ ስኳር ፋብሪካን ይዘናል።ኃይሎቻችን በነገሌ ቦረና ከመንግስት ወታደሮች ጋር ከባድ ውጊያ እያደረጉ ነው። ከአማራ ክልል የመጡ ሚሊሻዎች ኃይላችንን ለመዋጋት ወደ ምስራቅ ወለጋ እየገቡ ነው ሲል ይናገራል ኦነግ ሸኔ። በውጊያው ቦታዎችና አከባቢያቸው ያለው የኔትወርክ መጥፋት በኦነግ ሸኔ እንቅስቃሴ ላይ ብዙም ተፅዕኖ አልፈጠረም። ሲልም የድርጅቱ ወሬ አቀባይ ይናገራሉ ።
በመንግስት የሽብር ቡድን ተብሎ የተፈረጀው የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ኃይሉን እያጠናከረ በደቡብ ኦሮሚያ እንዲሁም በምራብ ኦሮሚያ እየተስፋፋ በንፁሀንም ላይ ግድያና ማሳደድ እየፈፀመ መሆኑን ከየአከባቢው የተፈናቀሉ ዜጎችና የራሱ የታጣቂው ቃል እቀባዮች ከሚለቁት ቪዲዮና መግለጫዎች ማወቅ ተችሏል። አራቱም ኦፕሬሽኖች ሙሉ በሙሉ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን በምዕራብ ኦሮሚያ ያለው የኔትወርክ መጥፋት በኦነግ ሸኔ እንቅስቃሴ ላይ ብዙም ተፅዕኖ አልፈጠረም በማለት የተዋጊዎቹ ቃል አቀባይ ይናገራል።
1 – የኦነግ ሸኔ ቡድን በጉጂ ቦረና ኢልማቂልጡ በሚል በከፈተው የጦርነት ዘመቻ በቁጥጥሩ ስር ባዋላቸው ምዕራብ ጉጂ ቡሌ ሆራ፣ መልካሳ ሰዳ፣ ገላና ሱሮ ባርጉዳ ‘ንዲሁም በምስራቅ ጉጂ ጉሚ ኤልዳሎ፣ ጉሮ ዶላ፣ ሳባ ቦሮ ዋዳራ እና ሊበን አከባቢዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሲያፈናቅል ከ300 ሰዎች በላይ መግደሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በቡልቡል ፣ ዳካ ቃላቲ ፣ ሙጋዮ ፣ ቦባ እና ሲሚንቶ ውስጥ ጉልህ ተሳትፎ ከተደረገ በኋላ በዚህ ወረዳ ውስጥ ካሉት 18 ከተሞች 16 ቱ በአሁኑ ጊዜ በኦነግ ስህኔ ታጣቂዎች ሥር ናቸው። በነገሌ ቦረና ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ስር ያሉ ስትራቴጂያዊ ቦታዎችን በመያዝ ቀጣይነት ያለው የታጣቂው ጦር. ክወናዎች አሉ። የኦነግሸኔ ኃይሎች በአዲስ አበባ – ሞያሌ መንገድ የተለያዩ ክፍሎች ላይ የፍተሻ ጣቢያዎችን ማሰማራታቸውን ቀጥለዋል። የሲብራ ኦዳ አዶላ ብርጌድ በዋዳራ ወረዳ በመንግስት ወታደሮች ላይ አዲስ ጥቃት በመክፈት ከሰሜን ምዕራብ ወደ ሲዳማ ግዛት የሚወስደውን መንገድ በመቁረጥ ተሳክቶላቸዋል።
2 – ቺሊሞ ደን ፣ ምዕራብ ሻዋ – በመንግስት ወታደራዊ ጥበቃ ላይ በተከታታይ የተደረጉ ጥቃቶች በአካባቢው የመንግስት ወታደሮች ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ምክንያት ሆኗል። አባይ ጮመን ወረዳ ሆሮ ጉዱሩ – ኦላ ከቀናት ከባድ ውጊያ በኋላ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካን እና አካባቢውን ተቆጣጥሯል። ቢሆንም ኦነግ ሸኔ ካወጣው ቪዲዮና መግለጫ በስተቀር ከነፃ ምንጮች ማረጋገጥ አልተቻለም ።
3 – በወለጋ ዞን ኦፕሬሽን ለገሰ ዋጊ በሚል የጦርነት ዘመቻ በዋዩ ቱቃ ወረዳ ውስጥ የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች ሽንፈት ደርሶባቸው ወታደራዊ ካምፓቸውን ጥለው ከፈረተጡ ከፊሎቹም ከኦነግ ሸኔ ጋር ከተቀላቀሉ በኃላ የፌዴራሉ ጦርና የአማራ ልዩ ኃይል በኪረሙ ፣ በአሙሩ እና በኡኬ ቃርሳ አከባቢዎች እንዲሰማሩ ተደርገው ነበር ። የስሀኔ ጦር መንግስት ካሰማራቸው ወታደሮች ጋር ውጊያ የገተመ ሲሆን ከ45 በላይ የአማራ ተወላጆችን በመግደልና የበርካታ ንፁሃንን ቤት በማቃጠል እንዲፈናቀሉ ያደረገ ሲሆን የምስራቅ ወላጋ ሰሜናዊ ክፍል ቁጥጥር ስር እንዳዋለው ታውቋል።
4 – በባሌና አርሲ በኦፕሬሽን ናዲ ገማዳ ሄባኖ ፣ ኮኮሳ አውራጃ ፣ የኦነግሸኔ ኮማንዶ ክፍል የመንግስት ወታደሮችን በመግደል ሲቪሎችን በማዋከብ እና ቤቶቻቸውን በማቃጠል ከፍተኛ ሽብር በመፍጠር ላይ መሆኑ ተሰምቷል። የአከባቢው ነዋሪዎች መሸሻቸው ታውቋል።