ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሦስት የመወሰኛ ም/ቤት ሴኔተሮች በኮሮናቫይረስ ተያዙ

በዩናይትድ ስቴትስ ሙሉ በሙሉ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሦስት የመወሰኛ ምክር ቤት ሴኔተሮች ኮሮናቫይረስ እንደያዛቸው ዛሬ አስታውቁ።

ሴኔተሮቹ የሚሲስፒው ሪፐብሊካን ሮጀር ዊከር፣ የኮሎራዶው ዲሞክራት ጃን ሂከንሉፐር እና ከሁለቱም ፓርቲ ያልሆኑት የሜይኑ ነጻው ሴነተር አንገስ ኪንግ ናቸው። ሦስቱም የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔተሮች ክትባቱን መከተባችን በቫይረሱ ምክንያት በጽኑ እንዳንታመም ረድቶናል…