ወደ ደብረ ታቦር ከባድ መሳሪያ ተወርውሮ እንደነበር ተሰምቷል

ዛሬ ወደ ደብረ ታቦር ከባድ መሳሪያ ተወርውሮ እንደነበር ተሰምቷል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ ዛሬ ወደከተማዋ የተወረወሩት የከባድ መሳሪያዎችን አስመልክቶ ፤ “ከባድ መሳሪያዎቹ ጠላት ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ ደብረታቦርን የማጥፋት ከፍተኛ ፍላጎት ማሳያ ነው” ሲሉ ገልጸውታል።

ዋና አስተዳዳሪው ፤ “ጠላት እየተመታ እግሬ አውጭኝ ብሎ እየፈረጠጠ ስለሆነ እንረጋጋ፤ አሁን ከወረወረው ውጭ ወደ ከተማችን ለመወርወር እንዳይችል እየተቀጠቀጠ ነው” ሲሉ አክለዋል።

በሌላ በኩል የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህወሓት ቡድን አባላት ሰርገው በገቡበት የጋሸና አካባቢ ሽንፈትን ተከናንበው ተደምስሰዋል ሲል አሳውቋል።

የሀገር መከላከያ የደቡብ ዕዝና ሌሎች የፀጥታ አካላት ባደረጉት ፈጣን ኦፕሬሽን ድል መገኘቱ ተገልጿል። ከ4 የሰሜን ወሎ ወረዳዎች ህወሓት ተጠራርጎ እንደወጣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።