የመራሒተ መንግሥቷ እጣ ፈንታ

መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ሰሙኑን በጀርመን ፖለቲካ መድረክ ቀላል ቀናትን አላሳለፉም። ባለፉት ሳምንታት ፓርቲያቸዉ ሰራቸዉ ስለተባለዉ ስህተት እንዲያምኑ መገደዳቸዉ፤ ፓርቲያቸው ባካሄደው የምክር ቤት አንጃ መሪ ምርጫ ላይ እሳቸው የሚደግፉትን እጩ ማስመረጥ አለመቻላቸው በሥልጣን የመቆየታቸዉን ነገር አዳጋች ሳያደርገው እንዳልቀረ ተገምቷል።…