የኮቪድ-19 ወቅታዊ ዓለም አቀፍ ይዞታ

ጃፓን ውስጥ የኮቪድ-19 ህሙማን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል። የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ዮሺሂዴ ሱጋ ሆስፒታል የሚገቡት በጽኑ የታመሙ ወይም ይጸናባቸዋል ተብሎ የሚያሰጉ የኮቪድ ህሙማን ብቻ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፥ የተቀሩት የኮቪድ ህሙማን በቂ የሆስፒታል ቦታ እስከሚገኝ ቤታቸው ራሳቸውን ለይተው መቆየት አለባቸው ብለዋል። ጃፓን ውስጥ በየቀኑ አስር ሺህ የኮቪድ ተጋላጮች…