በአክሱም ዩኒቨርስቲ ተመድበው ሲማሩ የቆዩ ተማሪዎችን ማስወጣት ተጀመረ

በአክሱም ዩኒቨርስቲ ተመድበው ሲማሩ የቆዩ ተማሪዎችን ማስወጣት ተጀመረ

* የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የማስወጣት ሂደት ተጠናቅቋል ተብሏል

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)በትግራይ ክልል በሚገኘው አክሱም ዩኒቨርስቲ ተመድበው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ከቆዩ ተማሪዎች መካከል፤ ግማሽ ያህሉ ትላንት ምሽት በአፋር ክልል ወደሚገኘው ሰመራ ዩኒቨርስቲ መግባታቸውን ተመላሽ ተማሪዎች ገለጹ።

የአክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ማስወጣት የተጀመረው በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎችን የመመለስ ሂደት ባለፈው አርብ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በአክሱም ዩኒቨርስቲ ተመድበው ሲማሩ የቆዩ ተማሪዎች ብዛት 3,500 እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ አስታውቀዋል። ከእነዚህ ውስጥ ትላንት ሰኞ ሐምሌ 26 ወደ አፋር ክልል የገቡት 1 ሺሕ 820 ተማሪዎች መሆናቸውን ተመላሽ ተማሪዎች ተናግረዋል።

አፋርን ከትግራይ በምታዋስነው አብኣላ ከተማ የሚኖሩ አራት የከተማው ነዋሪዎች፤ ተማሪዎችን የጫኑ ከ20 የሚበልጡ አውቶብሶች ትናንት ማምሻውን ከተማውን ሲያቋርጡ መመልከታቸውን ተናግረዋል። በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ያሉ የዓይን እማኞች በበኩላቸው የአክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በ28 አውቶብሶች ተጭነው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የደረሱት ትናንት ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ ነው ብለዋል።