በከሰላ ግዛት ከወንዝ ውስጥ ከ30 የሚልቅ አስክሬኖች መገኘታቸው አንድ የሱዳን ባለስልጣን አመለከቱ።

At least 30 corpses have washed up on the Sudanese banks of a river that abuts Ethiopia’s northern region of Tigray, according to two Ethiopian refugees and four Sudanese witnesses who told Reuters on Monday they had retrieved the bodies.

ሱዳን ከሰላ ግዛት የተገኙት አስክሬኖች ፦

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የሱዳን ባለስልጣን በከሰላ ግዛት ከወንዝ ውስጥ ከ30 የሚልቅ አስክሬኖች መገኘታቸው አመለከቱ።

ባለስልጣኑ ሟቾቹ በትግራይ ክልል ካለው ጦርነት የሸሹ ሳይሆኑ አይቀሩም ብለዋል። ገሚሱ በጥይት የተመቱበት ቁስለት ሌሎቹ እጆቻቸው እንደታሰሩ አስክሬኖቻቸው በወንዝ ላይ መንሳፈፉን ገልፀዋል።

ስማቸው ይፋ እንዲሆን ያልፈለጉት የሱዳኑ ባለስልጣን የግለሰቦቹ አሟሟት መጣራት እንዳለበት አመልክተዋል።

አስክሬኖቹን የተመለከቱ ሱዳን ሃምደያት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የጤና ባለሞያዎች በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተከዜ እየተባለ በሚጠራው ወንዝ ውስጥ ተገኙ የተባሉትን አስክሬኖች መመልከታቸውን ተናግረዋል።

The bodies were found in the Setit River, known in Ethiopia as the Tekeze, which is the current de facto borderline between territory controlled by Tigrayan forces and those controlled by Amhara forces allied with Ethiopia’s federal government. At a different point the river also separates Sudan from Ethiopia.

አስክሬኖቹን በቅድሚያ አሳ አስጋሪዎች የተመለከቱ ሲሆን በየአካባቢው ያሉ ስደተኞች ቢያንስ አስር የሚሆኑትን መቅበራቸውን አመልክተዋል ፤ ያም ሆኖ አብዛኞቹ አስክሬኖች ለማውጣት ሰሞኑን በነበረው ዝናብ ወንዙ በመሙላቱ አዳጋች እንዳደረገው Reuters ዘግቧል።