ሒውማን ራይትስዎች በሳዑዲ ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች 

በሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ተባብሶ የቀጠለው እንግልትና ስቃይ አሳስቦኛል ሲል ሂውማን ራይትስ ዋች ገለፀ። በድርጅቱ የፍልሰተኞች መብት ተመራማሪ ናድያ ሃርድማን እንዳስታወቁት በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በደል በተመለከተ ድርጅታቸው ለሳዑዲ መንግስት ሪፖርት ቢያቀርብም ምላሽ አላገኘም…