ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረገችው ወታደራዊ ትብብር በማንም ላይ ስጋት የሚፈጥር አይደለም – በኢትዮጵያ የሩሲያ ኢምባሲ

ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር እያደረገችው ያለው የወታደራዊ ቴክኒክ ትብብር ከሕዳሴ ግድብ ጋር እንደሚያያዝ ተደርጎ የሚሰራጩ ዘጋባዎችን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኢምባሲ ባሰራጨው መግለጫ አስተባብሏል።

የሁለቱ ሀገሮች ወታደራዊ ትብብር በማንም ላይ ስጋት የሚፈጥር እንዳልሆነ የገለጠው የኢምባሲው መግለጫ፣ ሩሲያ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር ጭምር ተመሳሳይ የትብብር ስምምነቶች እንዳሏት ገልጧል።

የግድቡ ውዝግብ የሚፈታው በሦስትዮሹ የመርሆዎች መግለጫ እና በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ እንደሆነ፣ በኅብረቱ ማዕቀፍ ስር አስማሚ መፍትሄ የመገኘት እድሉም ገና እንዳልተሟጠጠ እና የግድቡን ግንባታ ፖለቲካዊ ገጽታ መስጠት እንደማይጠቅም ኢምባሲው ገልጧል።

Image