ማንኛውም የተቀመጠውን መመሪያን የሚጥስ የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር ለሚደርሰው አደጋ ኀላፊነት ይወስዳል

ማንኛውም የተቀመጠውን መመሪያ የሚጥስ የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር ለሚደርሰው አደጋ ኀላፊነት እንደሚወስድ የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዴለው ቀደም ሲል ሰኔ 23/2013 ዓ.ም የአየር በረራ መረጃ ማሳወቂያ (NOTAM & AIP SUP) ቁጥር A0166/21 እና AIP SUP A04,2021) መተላለፉን አስታውሷል፡፡
በተላለፈው መመሪያ መሠረትም ማንኛውም የአውሮፕላን አብራሪም ኾነ ኦፕሬተር የተቀመጠውን መመሪያ ከጣሰ ለሚደርሰው አደጋ ኀላፊነት እንደሚወስድ ገልጿል።