የትግራዩ ጦርነት ሰሞኑን በአፋር ክልል በኩል 54 ሺህ ሰዎች ገደማ ማፈናቀሉ ታወቀ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

DW : ስምንት ወራት የቆየውና አሁንም ያለዕልባት የቀጠለው የትግራዩ ጦርነት ሰሞኑን በአፋር ክልል በኩል ተስፋፍቶ 54 ሺህ ሰዎች ገደማ ማፈናቀሉን የአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኤጄንሲ አስታወቀ። የኤጄንሲው ኃላፊ አቶ መሃመድ ሁሴን ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በአፋር ዞን አራት ውስጥ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ህወሃት ደርሷል ባሉት ጥቃት በተለይም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ 8 ወረዳዎች ግማሽ ሚሊየን ያህል ህዝብን ድጋፍ ሊያስፈልገው እንደሚችል አረጋግጠዋል። በጦርነቱ ተጎድተው በየቦታው ለወደቁና ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት አሁንም በቀጠለው ጦርነት መደናቀፉን ኃላፊው አክለዋል።