ጠላት ለሊቱን ተጉዞ ቀን ያስለቀቅነው ቦታ ይዞ እናገኘዋለን።ከጠላት ፊት ተፋጠን እንደር ስንል ከአለቆቻችን ፈቃድ አጣን። – የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
ኮረም ግንባር ከነበሩት የሰማሁት።
በአብዛኛው የቢቸና፣የማቸከል፣የደብረ ማርቆስ እና የውጫሌ ሚሊሻዎች በሁለት ዋና ዋና ጎራ ተከፍለን በኮረሙ ግንባር ተሰልፍን ነበር ይላሉ። በዚህ ግንባር ጠላት በእየቀኑ ይመጣል ከባህሩ አሻግረን ስናሳዳቸው ተመለሱ እንባላለን እንመለሳለን።(ባህር የሚሉት አሼንጌ ሐይቅን ነው። እኛ ትዕዛዝ ተቀብለን ወደ ካንፕ እንገባለን ጠላት ለሊቱን ተጉዞ ቀን ያስለቀቅነው ቦታ ይዞ እናገኘዋለን።ከጠላት ፊት ተፋጠን እንደር ስንል ከአለቆቻችን ፈቃድ አጣን።
ሳምንቱን እንዲህ ከሰነበትን በኋላ ቅዳሜ ጠላት ጠንከር ብሎ መግጠም ጀመረ።ግን ብዙም ሳይቆይ ከረፋዱ ላይ ሸሼ።እሁድ በማንሰማው ቋንቋ በመገናኛ የሚያወሩ አካላት ሲዋጉን ዋሉ።ጥቃት ስንሰነዝር ተው ወገን ነው እያለን ዋልን።
ሰኞ ቦታ ቦታ ይዘን ተቀምጠን እያለ የመከላከያ ሰዎች መጡና ውጡ አሉን አንወጣም ስንላቸው ከመኪና እየገቡ ወጡ። የመከላከያ ሰዎች እንደወጡ ቅንቡላ ካለንበት አካባቢ እያረፈ መፈንዳት ጀመረ።ልበሙሉው ባለመነፀሩ አዋጊያችን ቦታ እንድንቀይር አዘዝን ቀየርን።ቅንቡላው እኛ ወዳለንበት ዳገት ተከትሎ መፈንዳት ጀመረ።አዋጊያችን አካባቢውን ሲቃኝ ካለንበት ዳገት ጫፍ አርሶ አደር መስለው የተቀመጡ ሰዎችን ጠረጠራቸው መሰል የተወሰኑ ሰዎች ወደ ዳገቱ ጫፍ ላከ በዚህ ግዜ ቅንቡላው ይባሱኑ መዝነብ ጀመረ ግን ከዳገቱ ጫፍ ያሉትን ማዳን አልቻለም። አሁንም በትዕዛዝ ቦታ ቀየርን ቅንቡላው ግን ቀድሞ የነበርንበትን ተራራ መደብደቡን ቀጠለ።
በዚህ ሁኔታ እያለን ከእኛ በስተፀሐይ መግቢያ(ምዕራብ መሆኑነው) የነበሩ አብረውን የዘመቱ ጓዶች ወንድሞቻችነን ትተን አንሄድም ብለው ኑ ወጡ ወጡ ተብናል አሉን።ማነው ውጡ ያላችሁ የበላይ አካል ነው ተብሏል። ከዚያ በኋላ ወደ ካንፓችን ተመልሰን የነበሩነኑ ጓዞች(እቃ ማለት ነው) ይዘን ተጓዝን በመንገድ ላይ የመከላከያ መኪና ያልፈን ነበር። የሆነ ቦታ ሰንደርስ መኪና አገኘን ምሽት ቆቦ ገባን።የቆቦ ህዝብ እናት የሆነ ህዝብ ነው የሚል ምስጋና ተሰጥቶሃል።
በጦርነት ሳንሸነፍ የበላይ ትዕዛዝ እየተባለ ተመለስን።እሄው እንደ ምታየን አልደማን አልቆሰልን የታጠቅነው መሳሪያም ይሄው አሉኝ።
እውነትም ነው አንድም የቆሰለ ሚሊሻ አላየሁም። ሁሉም እንደታጠቁ ናቸው።