ከገዢው ፓርቲ በስተቀር ከሁሉም ፓርቲዎች በጣም ብዙ አቤቱታ ለቦርዱ ቀርቧል።

May be an image of 3 people, people sitting and outdoorsበአማራና ደቡብ ክልል የታዩ ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች’

የፖለቲካ ፓርቲዎች በየምርጫ ጣቢያው ታዛቢ ወኪሎቻቸውን አስቀምጠው ጉዳዩን የመታዘብ እና የማየት ፣ችግር ካላቸው ያን አስመዝግበው ወደፍርድ ቤት የሚሄዱ ከሆነም ያን አስመዝግበው ሰነዶቻቸውም ይዘው ክርክራቸውን የመቀጠል መሰረታዊ መብት አላቸው።

በዚህ ረገድ አብዛኛው ክልል ጥሩ ሁኔታ አለ ፤ ነገር ግን በሁለት ክልሎች በጣም አሳሰቢ በሆነ ደረጃ፣ በአንዱ (አፋር ክልል) በመለስተኛ ደረጀ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር ሁኔታ መመልከቱን ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

አማራ እና ደቡብ ክልሎች ላይ የፖለቲካ ፓርቲ እጩ ወኪሎች ከቦታ ቦታ በፈለጉበት አግባብ መንቀሳቀስ እየቻሉ እንዳልሆነ፣ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ፣ ባጅ እየተቀሙ እንደሆነ ፣ ወደ ጣቢያ ሊጠጉ የማይችሉበት ሁኔታ እየተፈጠረ እንደሆነ እጅግ በጣም ብዙ አቤቱታ ለቦርዱ ቀርቧል።

አቤቱታው ከገዢው ፓርቲ በስተቀር ከሁሉም ፓርቲዎች ነው ለቦርዱ የቀረበው።

የክልሎቹ አስተዳዳሪዎች ይህን ችግር እንዲያስተካክሉ እና እንዲፈቱ ቦርዱ አሳስቧል።

ቦርዱ፥ ችግሩ ካልተፈታ የምርጫ ሂደቱን እና የውጤቱን ታማኝነት ችግር ላይ እንደሚጥለው ሊታወቅ ይገባል ብሏል።

ምርጫ ቦርድ ክልሎቹ በአፋጣኝ ማስተካከያ እንዲያደርጉ የታችኛው የአስተዳደር ክፍል በተጨማሪ አንዳንድ ጊዜ የህግ አስፈፃሚዎች በፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች ላይ ፣ በእጩ ወኪሎች ላይ የሚፈፅሙት ከህግ ውጪ የሆኑ ድርጊቶችን አሁንኑ እንዲያቆሙ ሲል በጥብቅ አስጠንቅቋል።

Source – NEBE ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ