በቴሌኮም ማጭበርበር ድርጊት የተሳተፉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በቴሌኮም ማጭበርበር ድርጊት የተሳተፉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በቴሌኮም ማጭበርበር ድርጊት የተሳተፉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰዱን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

ኢትዮ ቴሌኮም እንዳመለከተው ከ3ሺህ በላይ የቴሌኮም ጥቅል አገልግሎቶችን ለ2ሺ135 ደንበኞች በህገወጥ መልኩ በመሸጥ ላይ የተሳተፈ አንድ የተቋሙ ሠራተኛ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡

ግለሰቡ ህገወጥ ድርጊቱ የፈጸመው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ሲሆን የተቋሙ የደህነት ቡድን ባደረገው ክትትል እጅ ከፍንጅ በመያዝ ለህግ አስከባሪ አካላት አስረክቧል፡፡

ከዚህ ህገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮ ቴሌኮም ሳይከፍሉ የቴሌኮም አገልግሎት የተመጠቀሙ 2135 ደንበኞችም አገልግሎት እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡

ኩባንያው በህገወጥ ቴሌኮም ተግባር የሚሳተፉ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ቀጣይነት ያለው ክትትል በማድረግና በማጣራት ተገቢውን እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አስታውቋል።

በህገወጥ መንገድ የቴሌኮም አገልግሎት የሚጠቀሙ እና ለመጠቀም የሚሞክሩ ደንበኞችን አገልግሎት እንደሚያቋረጥ የገለጸው ተቋሙ ከህግ እና ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በቀጣይ ህጋዊ እርምጃዎች እንደሚወስድም አመልክቷል።

ህዝቡ የቴሌኮም ማጭበርበር ተግባራት በሀገር ደህንነትና ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሱትን አደጋ በመገንዘብ ለጸጥታና ለህግ አስከባሪ ተቋማት ጥቆማውን በማቅረብ ህገወጦችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ኢትዮ ቴሌኮም ጥሪ አቅርቧል።