ሰሞኑን የምናየው ችግርም ባንዲራ ነው ብለን አንሸፋፍን። እሽቅድምድም ነው። (መንግስቱ ዲ .አሰፋ )

ፖለቲካ፣ ርዕዮት ዓለም እና ንትርኩ፣ አልፎም ግጭቱ እና መገፋፋቱ፣ የኢትዮዮጵያ ሃገር ግንባታ የታሪክ አረዳድ ተቃርኖዎች፣ የቡድን ፖለቲካ፣ ይባስ ብሎም ፕሮፓጋንዳ ጠፍቶኝ አይደለም። በደንብ አድርጌ እረዳለሁ።

ሰሞኑን የምናየው ችግርም ባንዲራ ነው ብለን አንሸፋፍን። እሽቅድምድም ነው። የፖለቲካ ትርከትን እና የሥልጣን ማዕከላዊ ቦታን ለማግኘት የሚደረግ ፍትግያ ነው። ግራ ዘመሙም እንዳለ ቀኝ ዘመሙም አለ። አብዮተኛም አድሃሪውም አለ። ስንቱ ሃገር ገብቶ የለ እንዴ? ስንቱ ተነፈሰ? ስንቱ በአየሩ በሞገዱ በድምፅና በምስል፣ በሰልፍና በስድብ፣ በፉከራ ሰማን ዐየን። ኧረ ደርጉም አለ። ድፍርስ ነው አልጠራም። ጥሩ ነው ይጠራል። ጊዜ ነው ዳኛው።

ከምንም በላይ ያስተዋልኩት አለመተዋወቃችንን ነው። ለመተዋወቅም ፍላጎት ስናሳይ አላየሁም። ብሔርተኝነት (ዘውጌውም ሆነ ሲቪኩ) የአንፃራዊነት ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ያው ነው፤ Limited loyalty ነው ሁለቱም። ሰብዓዊነት (HUMANITY) ማለት ሲቪክ ብሔርተኝነት አይደለም። INTERCHANGEABLY ስንጠቀም እና ሌላው ከሰብዓዊነት የሚያወርድ፣ ያኛው ደግሞ የሰብዓዊነት ፤እኩያ” እንደሆነ ሲቀርብ ስላየሁ ነው። ሁለቱም በተለያየ ደረጃ የተቀመጡ የውስን ቡድን ወገኝተኝነት ነው።

ለፖለቲከኛ ደግሞ ሁለቱም ድጋፍ ለማግኘት ሕዝብን የማደራጃ ኃይል ነው…ለኛ ማንነት ወይ ምንነት ይሆን ይሆናል።

ሌላ ሃሳዊ ነገር፦ ብሔርትኝነት (ሁለቱም ማለቴ ነው) ደግሞ ዘረኝነት አይባልም።

ግን ዘረኝነት ምንድነው? Racism የሚባለው ነገር እንዴት በሃገራችን ይኖራል? Racism መሠረት የሚያደርገው ራሱን የቻለ የRace ልዩነት መለኪያዎችን (Anthropometrics) አለው…እኛ ያው አንድ Race ነን ብዬ ነው…ቢያንስ የተማራችሁ ሰዎች በቃላት አጠቃቀም ግድፈት ትውልድን አትቅረፁ! ሌላ ጥናታዊ ሥም አውጡለት እንዳልል እንዲጠፋ ስለምፈልግ ሌላኛው ስሙን ማወቅ አልፈልግም።

ካለንበት ጊዜ እና ሁናቴ አንፃር ይሄ ሁሉ ግን ጥቃቅን ነው። በጣም ኢምንት!

~በሃገራችን ጉዳይ በእጅጉ የማንስመማ

~ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ኖሮን የማያውቅ

~ታሪክን ማውራት እንጅ መሥራት ያቃተን

~ዛሬም በበሬ እና ሞፈር የምናርስ

~ከዓለም ድሃ ሃገራት ተምሳሌት የሆንን

~8.4 ሚሊዮን የተራበ ዜጋ ያለን

~2.8 ሚሊዮን በግጭት ምክንያት የተፈናቀለ ዜጋ ያለን፣ በምግብና ውኃ፣ በመጠለያ እና ጤና እጦት የሚሰቃዩ ተፈናቃዮች ያለን (ከሶርያ በልጠን ከዓለም አንደኛ ሆነናል)

~የአየር ንብረት ለውጥ ከሚጎዳቸው ሃገራት አንዷ የሆንን

~የተፈጥሮ ሃብት እየተመናመነብን ያለን

~የሕዝብ ቁጥር ከቁጥጥር ውጪ እያደገ ከፖለቲካ ርዕዮት ዓለም አጀንዳ የማይገባበት ሃገር ያለን

~ከፍተኛ የተማረ እና ያልተማረ ወጣት የሥራ አጥ ቁጥር ያላት ሃገር ሆነን ሳለ

ዛሬ በትንሽ ትልቁ ስንባላ አንድ የሚታወቅ የ”SHARLOCK HOMES AND DR. WATSON”ን ታሪክ ያስታውሰኛል።

እንዲህ ይላል።

Sherlock Holmes and Dr Watson Go Camping

Sherlock Holmes and Dr. Watson decide to go on a camping trip. After dinner and a bottle of wine, they lay down for the night, and go to sleep.

Some hours later, Holmes awoke and nudged his faithful friend.

“Watson, look up at the sky and tell me what you see.”

Watson replied, “I see millions of stars.”

“What does that tell you?”

Watson pondered for a minute.

“Astronomically, it tells me that there are millions of galaxies and potentially billions of planets.”
“Astrologically, I observe that Saturn is in Leo.”
“Horologically, I deduce that the time is approximately a quarter past three.”
“Theologically, I can see that God is all powerful and that we are small and insignificant.”
“Meteorologically, I suspect that we will have a beautiful day tomorrow.”
“What does it tell you, Holmes?”

Holmes was silent for a minute, then spoke: “Watson, you idiot. Someone has stolen our tent!”

ምን ለማለት ነው?
እንጃ!

ሰናይ ቀን!