የብሔራዊ መግባባት እና እርቀ ሰላም ጉባዔ ጥሪ

የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ  መግባባት እና እርቀ ሰላም ጉባዔ በቀጣዩ ሩብ ዓመት ለመጥራት እቅድ መያዙ ተገለጸ። አምስት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንዳስታወቁት፣ በሀገር ቤት እና ከሀገር ውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ቡድኖች የሚሳተፉበትን ጉባዔ ባለፈው ነሀሴ ወይም ጳጉሜ በአዲስ አበባ ለማካሄድ ታስቦ ነበር።…