ትህነግ አንገት መቁረጡን ቀጥሏል፣ “ባንዳ” ያሏቸውን የእንድርታ ተወላጆች ረሽነዋል።

ጌታቸው ሽፈራው – ከሱዳን ወደ ትግራይ ሊሻገሩ ከነበሩት መካከል በውጊያ የተገደሉ አራት የትህነግ ታጣቂዎች አንገታቸው ተቆርጦ ነው የተገኘው። መከላከያ መንገድ ላይ የሞቱ አሉ ያላቸውም በውሃ ጥም ሞቱ የተባለው ትክክል አይደለም። አስከሬናቸውም አልተገኘም። ምርኮኞቹ ራሳቸውን ለማዳን የሰጡትን ቃል እውነት አድርጎ ነው የመከላከያ ሰራዊቱ ቃል አቀባይ የነገረን። እውነታውን የትህነግ አክቲቪስቶች ባንዳዎች እርምጃ ተወሰደባቸው ብለው ቀድመው ነግረውናል።
ከተማረኩት መካከል የተወሰኑት ሁመራ ሆነው ሲሰልሉ የነበሩም አሉበት። እነዚህ ሰዎች ናቸው ለትህነግ አክቲቪስቶች መረጃ እያደረሱ ባንዳ ላይ እርምጃ ወሰድብ ብለው የድል ዜና አስመስለው የሚያስፅፉት። ሁመራ አካባቢ ዘጠኝ ሰዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለው የፃፉትም ጦርነቱ በጀመረበት ወቅት ነው። “ባንዳዎች እርምጃ ተወሰደባቸው” የተባሉት ከሱዳን ወደ ትግራይ ለመሻገር ከመጡትና ሁመራና አካባቢው ቆይተው የተጨመሩትን ነው። እነዚህን ሰዎች የገደሏቸው የአማራ ፀጥታ ኃይልና መከላከያ ሰራዊቱ እየተከተላቸው መሆኑንና ከፊትም መንገድ እንደተዘጋባቸው ሲያውቁ “እነሱ መረጃ አውጥተው ነው፣ ጠቁመውብን ነው” በሚል ነው። መከላከያ ሲጠይቃቸው “በውሃ ጥም ሞተዋል” ያሉት ተጠያቂ ላለመሆን ነው እንጅ ጦርነቱ የተጀመረው ዘጠኝ ባንዳዎች ላይ እርምጃ ወስደናል ባሉበት ወቅት ነው። ሁመራ ከርመው ከሱዳን ከመጡት ጋር የተያዙ አሉ። ሁመራ ላይ ዘጠኝ ባንዳዎች እርምጃ ተወሰደባቸው የተባሉትም ከሁመራ ተነስተው ከሱዳን ከመጣ ጋር የተቀላቀሉ መሆናቸው ነው። እነዚህ እርምጃ የተወሰደባቸው የእነ ስብሃት ነጋው አረመኔ የትግራይ ፖለቲካ ባንዳ የሚላቸው የእንድርታ ሰዎች ስለመሆናቸው፣ ገና ፈርጀው እርምጃ ወሰድንባቸው ሲሉ ፅፈናል። ገና ጦርነቱ እንደተጀመረ፣ የትህነግ ኃይሎች ሳይያዙ።
መከላከያ በውሃ ጥም ሞቱ ያላቸውን ያወቀው ምርኮኞቹ ከሱዳን ስንት ሰው እንደመጣ ሲጠየቁ የተወሰኑት 304 አሉ፣ ቀሪዎቹ 315 አሉ። ሌሎቹ 320 ያህል ብለዋል። እና ሌሎቹ የት ሄዱ ሲባሉ በውሃ ጥም መሞታቸውን ተናግረዋል። እውነታው ግን ባንዳዎች እየተባሉ የተረሸኑ ናቸው። ሁመራ ሆነው ጠቁመውብናል ያሏቸውም ስም ዝርዝርም መያዛቸው ተገልፆአል። – ጌታቸው ሽፈራው