የቁልቁለት ጉዞው ይገታ!

የቁልቁለት ጉዞው ይገታ! – ሲራራ – Sirara
May be an image of 1 person and text that says 'c Easy Shelf TulipIna ሲራራ Jano Bank &LEZARd Setches, Dividers እፍይታ Coming Soon! "በሰላም ለመኖር ከፈለግህ ለጦርነት ተዘጋጅ በሁርሶ ማሰልጠኛ ለሁለተኛ ዙር የመሠረታዊ ውትድርና ስልጠና ተጀመረ kash ሲራራ ማተ ፍርገች የመሬትን ነገር መላ እንበል! ያልተገታው የዴሞክራሲ የቁልቁለት ጉዞው eEandg 0964434343 wwww.eandigt.com AUOITORIUMI'በአገራችን ስለ ብልጽግና እየተወራ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታትም ስለ ልማት እና ልማታዊነት ብዙ ተብሎ ነበር፡፡ ሆኖም እንኳን ሁሉንዐቀፍ ልማት የኢኮኖሚ ዕድገቱም አከራካሪ ሆኗል፡፡ ቢያንስ መቀጠል አለመቻሉን ሁላቻንም እናውቃለን፡፡ አሁንም ብልጽግናው ቀርቶብን መጀመሪያ የቁልቁለት ጉዟችን በተገታ በሚያስብል ሁኔታ ላይ የምንገኝ አገርና ሕዝብ ነን፡፡

ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች በተለየ መልኩ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት የነበራት ኢትዮጵያ በዘመነ ኢሕአዴግ በሕገ መንግሥት ደረጃ ዘውጌ ማኅበረሰቦች (ethnic groups) “የየራሳቸው ክልል እንዲኖራቸው” ሲደረግ፣ እያንዳንዱ ዘውጌ ማኅበረሰብ የራሴ ከሚለው ክልል ውጪ የማይገደው ብቻ ሳይሆን “ሌሎች” የእኔ ነው ወደሚለው ክልል ሲመጡ እንደ መጤ እንዲቆሩ ሆኑ፡፡ በዚህ ምክንያት በጊዜ ሒደት ማዕከላዊ መንግሥቱ እየተዳከመ ክልሎች ግን እየተጠናከሩና እየተለያዩ የተወሰኑ በሕዝብ ስም የሚምሉ አበጋዞች የሚቆጣጠሯቸው እንዲሆኑ ዕድል ከፍቷል፡፡
በዚህ ውጥንቅጥ ምክንያት ኢትዮጵያ እንደ ሕንድና ሌሎች ዴሞክራሲያዊ አገሮች ኅብረ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ የሆነ እና የሕግ የበላይነት የነገሠበት መትከል አልቻለችም፡፡ ከዚያ ይልቅ በሥልጣን ላይ ያለውም ሆነ ወደ ሥልጣን ለመውጣት የሚታገለው አካል ዘውጌ ብሔርተኝነትን የሥልጣን መወጣጫና ሀብት የመሰብሰቢያ መሣሪያ አድርጎታል፡፡ ስለሆነም ጠንካራና ዘመናዊ ማዕከላዊ መንግሥት እና የግለሰቦችና የቡድኖች መብት የተከበረባቸው ጠንካራና ዴሞክራሲያዊ ክልሎችን መገንባት አልተቻለም፡፡

የአገሮች ፖለቲካ እንዲሻሻልም እንዲበላሽም የሚያደርገው በሥልጣን ላይ ያሉት መንግሥት ፖሊሲ ነው፡፡ ከ66 አብዮት በኋላ በዚህች አገር ለነገሠው ግራ ዘመምና ጽንፈኛ ዘውገኛ አስተሳሰብ ምክንያት የሆነው የዐፄ ኀይለ ሥላሴ መንግሥት ራሱን ከጊዜውና አገሪቱ ከምትፈልገው ሁኔታ አንጻር አለማስተካከሉ ወይም ያን ለማድረግ ዳተኛ መሆኑ ነው፡፡ የደርግ መንግሥት የተከተለው አካሄድም ከእሱ በኋላ ለመጣው ቅጥንቅጥ ተጠያቂ ነው፡፡ አገሪቱ አሁን ለገባችበት አደገኛ የህልውና አደጋ የዳረጋት ደግሞ የኢሕአዴግ መንግሥት የተከተለው ፖሊሲ ነው፡፡ አሁን ያለው አመራር የአገሪቱ የፖለቲካ አካሄድ መስመር እንዲይዝ የማድረግ ቁርጠኝነት ካለው የማይችልበት ምክንያት የለም፡፡ እየተንከባለሉ የመጡ በርካታ ችግሮች መኖራቸው የሚታወቅ ቢሆንም የመንግሥት ሥልጣን የያዙት አካላት ቁርጠኞች ከሆኑ የአገሪቱ ችግር የማይፈታ ችግር አይደለም፡፡ በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ችግሮች የሚፈጠሩትም የሚፈቱትም በአመዛኙ የመንግሥት ሥልጣን በያዙ አካላት ነው፡፡

ኢትዮጵያዊያን ዜግነታችንን ከምር መውሰድና የዜጋ ተግባር መፈፀም ይገባናል፡፡ የአንዲት አገር ዜጋ ዜጋ ነው የሚባለው የዜያችን አገር ትዕምርቶች ሲያከብር፣ ለዚያች አገር ሉዓላዊነት፣ ሁለንተናዊ ሰላምና ደህንነት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ድረስ ለመክፈል ሲዘጋጅና ይህንን ዝግኙነቱንም በአገሪቱ ዋና ዋና ሰነዶች (ፓስፖርት ወዘተ…) አምኖ ሲቀበልና ሲያረጋግጥ ነው፡፡ የአንዲት አገር ዜጋ ዜጋ ነው ሊባል የሚችለው የመምረጥና የመመረጥ መብቱ ሲረጋገጥ ነው፡፡ ይህ ብቻ ግን አይደለም፡፡ ዜግነት ከዚህም በብዙ መለኪያዎች የላቀ ጉዳይ ነው፡፡

የዜግነትን ጥቅም መረዳት የምንችለው ዜግነት ባላገኘንበት አገር ስንነኖር ነው፡፡ ዜግነት የሚሰጠውን ጥቅምና ክብር መረዳት የሚቻለው ወደ ሌሎች አገሮች ስንሄድና ምን ያህል ከለላ የሌለን መሆኑን ስንረዳው ነው፡፡ ዜግነት ብዙ መብቶችን የሚያጎናጽፍ ነገር የመሆኑን ያህል ከዜጎችም ብዙ ነገር ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያዊያን የዜግነት ኀላፊነትን በመወጣት ረገድ ብዙ፣ በጣም ብዙ ይቀረናል፡፡ ዜግነትን እንደዘበት የምንቆጥረውም ብዙዎች ነን፡፡ የአገራችን ሉዓላዊነት እንዲከበር ቀናዒ የሆንነውን ያህል የሕዝብ ሀብትን በመጠበቅና በመንከባከብ ረገድ በጣም ደካሞችና ግለኞች ነን ማለት ይቻላል፡፡ የውጭ ጠላት አገራችንን እንዳይደፍራት መስዋዕት ለመሆን የማናመነታ ቢሆንም የአገራችንና የዘውጋችን ፈላጭ-ቆራጮች እንደፈለጉ እንዲፈነጩብን ዕድል የምንሰጥ መሆኑ ትልቅ ውድቀት ነው፡፡ በነጻነት የመደራጀት፣ ሐሳባችን የመግለጽ፣ የመምረጥና የመመረጥ መብታችንን ለመጠቀም የምናደርገው ጥረት በጣም ደካማ ነው፡፡

የአገራችንን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ የማናመነታ ብንሆንም ከድህነት የተላቀቀች፣ ሥነ ምኅዳሯ የተጠበቀ እና የለማች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የምናሳየው ተነሳሽነት በጣም ደካማ ነው፡፡ በጥቅሉ ዜጎች እንደ ዜጋ መሥራት ያለብንን ሥራ እና መወጣት ያለብንን ኀላፊነት በሥልጣን ላይ ላሉ አካላት ወይም ለተወሰኑ ቡድኖች የመስጠት ችግር ይስተዋልብናል፡፡ “መንግሥት አባት ነው፤ መንግሥት መሐሪ፤ ቻይ/ታጋሽ ነው” የሚል አስተሳሰብ ያለን ሕዝብ ነን፡፡

ዜግነት ትልቅ መብት የሚያጎናጽፈውን ያህል ኀላፊነቱም በጣም ከባድ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን የዜግነት መብታችን በመጠቀም እና ኀላፊነታችንን በመወጣት ረገድ ብዙ፣ በጣም ብዙ ይቀረናል፡፡ ታሪካችን ብቻ ሳይሆን አሁን ያለን የፖለቲካ ዘይቤ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያዊያን ራሳችንን በጥቅምና በሲቪክ ማኅበረሰብ እያደራጀን መብታችንና ጥቅማችን ከማስከበር ይልቅ ብዙ ነገሮችን ከመንግሥት የመጠበቅ ባህል አለን፡፡ እያንዳንዱ ዜጋ እንደ ዜጋ ተቆጥሮ ለመብቶቹና ለጥቅሞቹ መከበር በቁርጠኝነት ሲንቀሳቀስ አይታይም፡፡ በአገራችን አምባገነኖች ለዘመናት እንዲፈነጩ ዕድል የሰጠው ይህ የሕዝባችን አስተሳሰብ ነው፡፡ በመንግሥት ላይ ልጓም የማያበጅ ሕዝብ፣ የራሱን ዜግነት ኀላፊነት የማይወጣ ሕዝብ፣ ይልቁንም ሁሉንም ከመንግሥት የሚጠበቅ ሕዝብ የትም አይደርስም፡፡ ለዘመናት የአንባገነኖች መፈንጫ ሆነን የኖርነው የዜግነት መብትና ግዴታችንን ጠንቅቀን አውቀን እንደ ዜጎች ስላልተንቀሳቀስን ነው፡፡

በአገራችን በጥፋቱ የሚወነጀለው፣ በልማቱ ጊዜም በብቸኝነት የሚወሰደው በሥልጣን ላይ ያለው አካል ወይም የየዘውጌ ማኅበረሰቡ መሪ ነኝ የሚለው አካል ነው፡፡ ይህ የዜጎችን ወሳኝነት ሚና የሚያሳንስ አስተሳሰብና አካሄድ እስካላተስተካከለ ድረስ በአገራችን ሁሉም ሰው በእኩልነት ሊኖር የሚችልበት ዕድል የለም፡፡