የግድቡን 2ኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች እንደማይሳካላቸው አውቀው ተስፋቸውን ሊቆርጡ ይገባል – የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት

May be an image of 2 people, military uniform and outdoorsለአገራችን ሰላምና ለህዳሴው ግድባችን ዕውን መሆን የማንከፍለው መስዋዕትነት የለም ሲሉ በቀጣናው ተልዕኳቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙ የሠራዊት አባላት ተናገሩ።
አባላቱ ሰላማችንም ሆነ ልማታችን በውጪ ኃይሎች ፍላጎትና በውስጥ ባንዳዎች ተላላኪነት ለአፍታም ቢሆን አይደናቀፍም ብለዋል።
አባላቱ አክለውም ከአበው የወረስነው የጀግንነት ታሪክ በእኛ ትውልድም ይደገማል፤ ህዝብና መንግስት የሰጡን ተልዕኮም ይሳካል በማለት ተናግረዋል።
የግድቡን ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች እንደማይሳካላቸው አውቀው ተስፋቸውን ሊቆርጡ ይገባልም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
መላው ኢትዮጵያውያን ተስፋ የጣሉበትን ታላቁ የህዳሴ ግድብን ከማናቸውም ጥቃት ለመከላከል ተልዕኮ ተቀብለን በቀጣናው መሰማራታችን አስደስቶናል፤ ለስኬታማነቱም ዝግጁነታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
May be an image of outdoors
May be an image of one or more people, tree and outdoors