ጀኔራል ኃይሌ መለሰ አርፈዋል

 ጀኔራል ኃይሌ መለሰ አርፈዋል

May be an image of one or more people and people standingበ1983 ዓ.ም. “እናት ሀገሬን ለወያኔ ትቼ አልሄድም” በማለት ፊቱን ወደ ጫካ ያዞረውና የሰሜኑ ግንባር ጀኔራሎች ወደ መኻል ሀገር ሲሸሹ፣ እርሱ ደቡብ ጎንደር ጫካ ገብቶ ወያኔን ከጀርባ በደፈጣ ውጊያ የገጠመው ጀኔራል ኃይሌ መለሰ… ከ1983 እስከ 1989 ዓ.ም ከስሜን ተራሮች እና ሸለቆዎች በስሙ ሳይቀር ወያኔን ያሸበረ ጀግና ነበር።

ደብረታቦር፣ ሀሙስ ወንዝ ከሚባለው አካባቢ የተወለዱት ጀኔራል ኃይሌ መለሰ፤ ደርግ ጎንደርን ሰሜን እና ደቡብ ብሎ ሲከፍል የደቡብ ጎንደር አስተዳደሪ ሁነው ተሾመውም ነበር።

በግንቦት 1983 ማግስት ፈጽሞ የማይታሰበውን ያሰበ ብቸኛው ከፍተኛ የጦር መኮንን… ባሕር ዳር በወያኔ በተከበበች ሰዓት ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ሔሊኮፕተር ልከው ከባሕርዳር እንዲወጣ ሲጠይቁት፣ “እናት ሀገሬን ለወያኔ ትቼ?” በማለት ፊቱን ወደ ጫካ ያዞረው ጀኔራል ኃይሌ መለሰ የ69ኛ ብርጌድ ጦርን መርተው የሱማሌ ወራሪ ደምስሰው ጅጅጋን ተቆጣጥረዋል።

ጀኔራል ኃይሌ መለሰ ከወረታ እስከ ባህርዳር በተደረገው ጦርነት በ1983 ዓ.ም ሰባት ጊዜ ሰባት ቦታ ላይ ቆስሎ ነበር። በኋላ የነገሩን ማለቅ ስለተረዱ በቀጥታ በታንኳ ተሻግረው ዘጌ አርፈው እንደገና ሌላ ታንኳ ይዘው እብናት ነው የገቡት።

እብናት ገብተው ህዝቡ ትጥቁን እንዳይፈታ “መጥቸልሃለሁ ትጥቅህን አትፍታ” ነው ያሉት። ህዝቡን እና ብዙ ሽምቅ ተዋጊዎችን አደራጅተው እየተዋጉ ለ5 ዓመታት ያክል ሲያዋጋ ቆይቷል።

May be an image of 1 person and textበዚያን ሰዓት ጀኔራል ኃይሌ መለሰ እጄን አልሰጥም ብለው፣ በአዲስ አበባ አቋርጠው ቀጥታ ወደ ኬንያ ወጡ። ከኬኒያ እንደገና ሱዳን ገብተው የሽምቅ ውጊያ ጀመሩ።

በወቅቱ ሱዳን አሳልፋ እንድትሰጣቸው የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ እና ክንፈ ከፍተኛ ጥረት አድርገው ነበር። ጀኔራል ኃይሌ ተላልፈው ሳይሰጡ ወደ ኒውዚላንድ ተሻገሩ።

እኒህ ለጠላት እጃቸውን ሳይሰጡ በዱር በገደል፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ዓለም ሁለገብ ትግል በማድረግ ፤ በአዋጊነትና በተዋጊነት የሚታወቁት ጀግናው ጀኔራል ኃይሌ መለሰ ከአውስትራሊያ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው፣ ባህርዳር አርፈው ሳለ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።

አስክሬናቸው ቅዳሜ በማርሽ ባንድ ከባህርዳር ተሸኝቶ፣ እሁድ ደብረ ታቦር ከተማ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ይፈጸማል።