ከሱዳን ወልቃይትን አቋርጦ ትግራይ ለመግባት ያቀደው ኃይል በዓከር ላይ በተደረገ ጦርነት አብዛኛው ተገድሏል።

በኮ/ል ባሕረ መሪነት፣ በሻምበል ተክላይ ምክትል አዛዥነት፣ ኢንስፔክተር ባየሁ ስለሽና ሌሎችም አስተባባሪነት ከሱዳን ወልቃይትን አቋርጦ ትግራይ ለመግባት ያቀደው ኃይል በዓከር ላይ በተደረገ ጦርነት አብዛኛው ተገድሏል። ከተረፉት መካከል አብዛኛዎቹ እጃቸውን ሲሰጡ፣ የተወሰኑት ከበባ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
ትህነግ ተስፋ ሲያደርግበት የቆየው ሱዳን ውስጥ ስልጠና ሲወስድ የነበረውን ኃይል ነው። ይህ ኃይል ሰሞኑን በወልቃይት በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ ሲል ድል ሆኖ መንገድ ላይ ቀርቷል። የወልቃይት ጠገዴ ገበሬ፣ ከአማራ ልዩ ኃይልና ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር ሆኖ መንገድ ላይ አስቀርቶታል።
በኮ/ል ባሕረ መሪነት፣ በሻምበል ተክላይ ምክትል አዛዥነት፣ ኢንስፔክተር ባየሁ ስለሽና ሌሎችም አስተባባሪነት ከሱዳን ወልቃይትን አቋርጦ ትግራይ ለመግባት ያቀደው ኃይል በዓከር ላይ በተደረገ ጦርነት አብዛኛው ተገድሏል። ከተረፉት መካከል አብዛኛዎቹ እጃቸውን ሲሰጡ፣ የተወሰኑት ከበባ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
ከ304 በላይ የሰው ኃይል የነበረው ይህ ቡድን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ ለብሶ ወደትግራይ ሊሻገር ሲል ነው የተመታው። ከሱዳን መድሃኒት፣ ስንቅና መሳርያዎችን ይዞ ወደ ትግራይ ሊሻገር አስቦ እንደነበር ነው የተገለፀው። ቡድኑ ከ230 በላይ ዘመናዊ የመገናኛ መሳርያዎችን ይዞ መገኘቱም ተገልፆአል።
የሚገርመው ይህ ኃይል መመታቱን ቀድመው የሰሙት የትህነግ አክቲቪስቶች፣ ትህነግ ሰራዊቱ ላይ ድል እንደተቀዳጀ አድርገው ዜና ሲሰሩ ሰንብተዋል። ትህነግ የመገናኛ መሳርያ እጥረት ገጥሞታል። የመድሃኒት እጥረት ገጥሞታል። ይህ ኃይል ትግራይ ቢደርስ ተአምር ይሰራልኛል ብሎ እየጠበቀ ነበር። ወልቃይት ላይ ቀርቷል። Getachew Shiferaw