የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የውክልና ተልዕኮ አስፈፃሚነት ውስጥ መግባቱን አሳይቷል

የአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለውጭ ሀገር ሚዲያዎች የሰጡት መገለጫ ሲዳሰስ !

የመግለጫው ዋነኛ ጉዳዮች የነበሩት ፦

-የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር

– የሱዳን ወረራ እና ያልተገባ ጫና

– 6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ

የታላቁ የህዳሴ ግድብን ግንባታ በተመለከተ ግብፅ በውሃ ላይ ምንም አበርክቶ ሳይኖራት እያሳደረች ያለው ጫና ተገቢነት እንደሌለው አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ አሁንም ድርድሩን በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ማስቀጠል እንደምትቀጥል አሳውቀዋል።

አምባሳደር የተናገሩት ምንድነው ?

“ግብፅ ሁሌ ጊዜም የምትናገረው በሀገሯ ድርቅ በሚከሰትበት ጊዜ ከግድባችን ልንለቅላት ስለምንችለው የውሃ መጠን መጨመር ነው። ይህ ማለት እነሱ የውሃ ባንክ ይሆናሉ።

ውሃ ካለህ ብቻ ነው መልቀቅ የምትችለው ግብፅ በድርቅ ስትጋለጥ ከግድቡ ስለሚለቀቅላት የውሃ መጠን እያወራች በሌላ በኩል ግድቡ እንዳይገነባ እና እንዳይጠናቀቅ ለምን ትሰራለች ? ለምን እንቅፋት ትሆናለች ? ይህ እርስ በእርሱ የሚቃረን ነገር ነው። በዚህ ሁኔታ የውሃ ባንክ ሊሆኑ ነው። የውሃ ባንክ የሚያደርጋቸውን ግድብ ለምን ይቃወማሉ ? ይህ ማንንም ሰው የሚያስገርም እና ጥያቄ እንዲያነሳ የሚያደርግ ነው።

በድጋሜ ጉዳዩን ግልፅ ለማድረግ እኛ በግድቡ አሞላል ሂደት ላይ እና በአሞላሉ ላይ ስምምነት ለመፈራረም ይሁንታ ሰጥተናል ስለሆነ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ ማድረግ አጋዥ አይሆንም። ማንንም አያግዝም የጀመርነው ሂደት መቀጠል ብቻ ነው የሚረዳን”

አምባሳደር ዲና የሁለተኛው ዙር ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። ግብፅ እና ሱዳን በዚህ ላይ ስምምነት ካልደረሱ ምን ይሆናል ተብለው የተጠየቁ አምባሳደር ዲና ተከታዩን ምላሽ ነው የሰጡት ፦

“በ3ቱ ሀገሮች በ2015 በሱዳን ካርቱም በተፈራረሙት የመርሆች መግለጫ መሰረት የግድቡ ሙሌት የግድቡ የስራ ሂደት አካል ነው። ስለዚህ የውሃ ሙሌቱ የግድቡ አካል ነው። ግድብ ከገነባህ ውሃ መሙላትህ እርግጥ ነው፤ ያ ነው ሊሆን የሚችለው ፤ በመጀመሪያው ዙር የግድቡ ሙሌት የሆነውም ይኸው ነው። አሁንም ተስፋ የምናደርገው በአሞላሉ እና በሂደቱ ላይ እንደምንስማማ ነው።”

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብን አስመልክቶ ሱዳን ከሰሞኑ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ላይ የባለቤትነት ጥያቄን ማንሳቷን አውግዘዋል።

በተለይ የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የውክልና ተልዕኮ አስገፃሚነት ውስጥ መግባቱን አሳይቷል ብለዋል።

አምባሳደር ዲና በዚህ ጉዳይ ይህን ነው ያሉት ፦

“የኢትዮጵያ ህጋዊ የግዛት ወሰን ላይ በዚህ ሁኔታ የይገባኛል ጥያቄ ማንሳቱ ሱዳንንም ቀጠናውንም ኢትዮጵያንም የሚጠቅም አይደለም። ኢትዮጵያ ጉዳዩን አሁንም በሰላም እንዲፈታ ግፊት ማድረጓን ቀጥላለች ሆኖም ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዋጋ እንሰጣለን። አክብሮትም አለን ነገር ግን ወታደራዊ ክንፉ እያደረገ ያለው ነገር የሱዳንንም ሆነ በቀጠናው ያለ የማንንም ፍላጎት ሳይሆን በውክልና ያልተገባ ጫና ማሳደር ነው።

በሌላ በኩል ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንደሚነገረው በሁለቱ ሀገራት መካከል ግጭት መፈጠሩን በተመለከተ መስሪያ ቤታቸው መረጃው እንደሌለው ተናግረዋል።

የአውሮፓ ህብረት ከሰሞኑን ምንም አይነት መሳሪያ እንዳያስገባ በኢትዮጵያ መንግስት መከልከሉ ፣ የምርጫ ውጤት ቀድሜ እኔ ይፋ ላድርግ በሚል ያቀረበው ቅድመ ሁኔታ ውድቅ ስለተደረገበት የምርጫ ታዛቢ አልክም ብሎ ነበር።

አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው እንዳሉት ከትላንት ጀምሮ የአውሮፓ ህብረት የባለሞያዎች ቡድን ለመላክ መስማማቱን አሳውቀዋል።

አምባሳደር ዲና የተናገሩት ፦

” የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እንደማይልክ ቢያሳውቅም ከትላንት ጀምሮ የባለሞያ ቡድን እንደሚልክ ተስማምቷል። የቴክኒክ ባለሞያውም ይላኩ ኃላፊዎችን የሚላኩት ታዛቢዎች ናቸው ይህን ነው ያሉት።”


[መረጀው የጋዜጠኛ ሰለሞን ሙጬ (ዶቼ ቨለ ሬድዮ) ፣ ፎቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር]