የጅግጅጋ ዩንቨርስቲ ውስጥ ሳይገነባ ተገንብቷል ተብሎ አየር ላይ የጠፋው ሕንፃ ጉዳይ ጥያቄ አስነስቷል።

 

የጅግጅጋ ዩንቨርስቲ ውስጥ ሳይገነባ ተገንብቷል ተብሎ አየር ላይ 100% የጠፋው የዩኒቨርስቲ ሕንፃ ጉዳይ ጥያቄ አስነስቷል።

የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ G+4 ህንፃ ለማሰራት ORRIX construction plc ከሚባል ድርጅት ጋር በ16 ሚሊየን ብር ይዋዋላል ። በዚህም መሰረት ተቋራጩ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስፈልገውን ቅድመ ክፍያ ለማግኘት የሚያስፈልገውን የቅድመ ክፍያ ጋራንቲ ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያመጣል ። እዚህ ላይ የተለመደው አሰራር ለአንድ ተቋራጭ የሚከፈለው ቅድመ ክፍያ ከሃያ ፐርሰንት የማይበልጥ ሲሆን እሱም የሚሰጠው ተቋራጩ ባቀረበው ፕሮፖዛል መሰረት መሆን ነበረበት ዩኒቨርሲቲው ግን ባልተለመደ ሁኔታ ለዚህ ተቋራጭ የከፈለው ቅድመ ክፍያ ከ100 % በላይ ነው ። ማለትም ህንፃውን ለመስራት የተዋዋለው 16 ሚሊየን ብር ሆኖ ሳለ ባልታወቀ ምክንያት ተቋራጩ ከንብ ባንክ አመጣሁት ባለው የ16 ሚሊየን ብር የ advance payment guaranty መሰረት ለስራው ከሚከፈለው ብር በላይ ነበር የተከፈለው ።

አስገራሚው ነገር ገና ነው ። ሲጀመር ኦሬክስ ኩባንያ ከንብ ባንክ ያመጣው የ22 ሚሊየን ብር የቅድመ ክፍያ ዋስትና በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የማይታወቅ ፌክ ዶክመንት መሆኑ ነው ። ያ ማለት ድርጅቱ ለወሰደው ክፍያ ዋስታና የሚሆን አካል የለም ማለት ነው ። ኩባንያው አንደኛ ሊከፈለው የሚገባው 20% ቅድመ ክፍያ መሆን ሲገባው ከመቶ ፐርሰንት በላይ ክፍያ ወስዷል ። ሁለተኛ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ስም የተወሰደው ቅድመ ክፍያ በሃሰት በተዘጋጀ የዋስትና ሰነድ ነው ። ሶስተኛውና በጣም አስገራሚው ጉዳይ ደግሞ የህንፃው ፕሮግረስ ዜሮ ፐርሰንት መሆኑ ነው ። ምን ማለት ነው ? ምንም አይነት የህንፃ ግንባታ ስራ አልተጀመረም ።