የነደፉት ያስተጋቡት የሻጥር የሃሰት ወንጀሉ ወደነሱ ይዞራል – አሸባሪ የተባለችው አለም አቀፍ ሞዴሊስት የሐረርወርቅ ጋሻው

አሸባሪ የተባለችው ሞዴሊስት የሐረርወርቅ ጋሻው በፌስቡክ ገጿ በሽብር ወንጀል እፈልጋታለሁ ላለው የኢትዮጵያ መንግስት መልስ ሰጥታለች።

በኔ ላይ የሃሰት ውንጀላ ብሎም የፍርደገምድል ፍርድ መነዛት በዳላስ ሳይቀር የተፈጸመ ነው በትሩ በሚባል ገንዘብ ወዳድ ተቀነባብሮ።

ሙርከኛ ላስለቅቅ ጦር ሜዳ ስወርድ፣ የጦር ሃይል መስርታ ኢትዮጵያን ለመውጋት በጦር መሪነት ከሻቢያ ጋር በመተባበር ልትወጋን ነው ብሎ መለስ ካወጀው የተለየ አይደለም የአብይም። ማለት በሃሰት እኔን መወንጀል። መለስ ሙርከኞች ኢትዮጵያ የሏትም ባለው አፉ፣ ባይኑ ሲያይ በጆሮው ሲሰማ በብስጭት ተነስቶ አንድ ኢትዮጵያ ለሚባለው ሬዲዮ ገንዘብ መድቦ ሃሰቱን አስነሰነሰ።

ሃቅሓቁ በኔ እጅ ስለነበረ፣ የመለስ ውሸት አከተመ። የኔ የማይበተዝ ሃቅ ግን ዘለዓለም ይኖራል። ያሁንም በሃሰት በማላውቀው መወንጀሌን በብርሃኑ ነጋ፣ በነአመን, እዝቅኤል እስክንድር ፣ አክሎግ ቢራራ፣ ታማኝ በየነ፣ ወደፊትም ስማቸውን በምገልጸው አቀነባባሪነት ለቀረበብኝ የአብይን መንግስት ተንተርሰው የቀናት ጉዳይ ነው ። የነደፉት ያስተጋቡት የሻጥር የሃሰት ወንጀሉ ወደነሱ ይዞራል።

ያንበሳ ልጅ ነኝ የአንዲት የኢትዮጵያ። ከኣመርቲካን መሪ ጋር ያለኝ ብሎም በተግባር ከኣሜሪካን ጋር እየሰራሁ ያለሁት ኢትዮጵያን አንድነት ለማስከበር የሕዝቧንም መጨፍጨፍ ለማስቆም፣ አሟቸዋል በጣም። ጥሉ ቀጥሏል ኢትዮጵያ☝🏾