ለኢትዮጵያ አንድነት/የግዛት አንድነት ቁርጠኛ መሆናችንን እናረጋግጣለን – የG7 ስብሰባ

የG7 ስብሰባ በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን አለ ?https://assets.publishing.service.gov.uk/government/uploads/system/uploads/attachment_data/file/983631/G7-foreign-and-development-ministers-meeting-communique-london-5-may-2021.pdf

G7 Foreign and Development MinistersMeeting Communiqué

                             London, May 5, 2021

– አሁንም በትግራይ ያለው ሁኔታ ፣ የቀጠለው ግጭት እና የሰብዓዊ መብትና የሰብዓዊ ድጋፍ ቀውስ በእጅጉ ያሳስበናል ብለዋል።

– የሲቪሎች/የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ፣ የሴቶች አስገድዶ መደፈር ፣ የወሲባዊ ብዝበዛ ሌሎችም ፆታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶችን አውግዘዋል።

– የሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ቅርሶችን መውደም እና መዘረፍ አውግዘዋል።

– በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች እና የኤርትራ ስደተኞችን በግዳጅ ማፈናቀልን አውግዘዋል።

– በኢሰመኮ እና በUN የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር መካከል የተፈፀሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት የተደረገውን ስምምነት በደስታ ተቀብለዋል።

– ሁሉም ወገኖች በፍጥነት ግጭት እንዲያቆሙ፣ የዜጎችን ደህንነት እንዲያረጋግጡ፣ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ህጎችንና የሚዲያ ነፃነት እና ተደራሽነትን እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

– የሰብዓዊ ጥሰት እና ፆታዊ ጥቃቶችን የፈፀሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

– የውጭ ሀይሎች በትግራይ መኖራቸውን እጅግ የሚረብሽና መረጋጋት የሚያሳጣ መሆኑን ገልፀዋል።

– የኤርትራ ኃይሎችን ከትግራይ ለማስወጣት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስታት የሰጡትን መግለጫ እንደሚቀበሉ ገልፀው፤ ነገር ግን ማስወጣቱ ገና አለመጀመሩ እንዳሰጋቸው ገልፀዋል። የኤርትራ ወታደሮችን የማስወጣት ሂደቱ መፋጠን አለበት ብለዋል።

– በትግራይ ክልል ሁሉን አቀፍ ግልፅ የሆነ የፖለቲካ ሂደት እንዲፈጠር ጥሪ አቅርበዋል።

– ዛሬም ለኢትዮጵያ አንድነት/የግዛት አንድነት ቁርጠኛ መሆናችንን እናረጋግጣለን ብለዋል።

– በመጨረሻም፦ በኢትዮጵያ ተአማኒ ምርጫና ብሄራዊ እርቅ እንዲኖር ለማስቻል ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።