የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት የጄኖሳይድ ኮንቬንሽንን መሠረት ባደረገ መልኩ ኃላፊነት የመውሰድ ግዴታ እንዳለበት ማወቅ አለበት – እንግሊዝ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ የትግራይ ክልልን በሚመለከት አርብ ዕለት ባወጣው ሪፖርት የአገሪቱ መንግሥት በክልሉ ያለውን ግጭት ለማሰቆም በተቻለው ሁሉ የዲፕሎማሲ አማራጮችን መጠቀም እንዳለበት ገለፀ።

ፓርላማው የዩኬ መንግሥት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚካሄደውን ግጭት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማስቆም ኃላፊነት እንዳለበት ጨምሮ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራሉ መንግሥት የትግራይን ክልልን ያስተዳድር የነበረው ሕወሓት የሰሜን እዝን ማጥቃቱን ተከትሎ ወደ ግጭት መግባቱ ይታወሳል።

የፌደራል መንግሥቱ “ሕግ ማስከበር” ሲል በሚጠራው በዚህ ዘመቻ የክልሉን ዋና ከተማ፣ መቀለ ከተቆጣጠረ በኋላ የዘመቻውነ መጠናቀቅ ቢገለፅም አሁንም በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች ግጭቶ ች እየተካሄዱ መሆኑን መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስታውቀዋል።

በትግራይ ክልል ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን እና 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የመንግሥት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መረጃ ያሳያል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለያየ ጊዜ በትግራይ ጦርነት የኤርትራ ወታደሮች መሳተፋቸውን በመግለጽ ጦሩ በአስቸኳይ ትግራይን ለቅቆ እንዲወጣ ቢወተውትም የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ተሳትፎውን ሲያስተባብሎ ቆይተዋል።

በስተመጨረሻም የኤርትራ ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ያለፉት የደህንነት ስጋት ስላለባቸው መሆኑን በመግለጽ እንደሚወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አረጋግጠዋል።

ይህንንም ተከትሎ የኤርትራ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጦሩን እንደሚያወጣ መግለጹ ይታወሳል።

የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ምን አለ?

በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ቁልፍ ምክንያቱ በክልሉ ያለው ግጭት ነው ሲል ፓርላማው አትቷል።

በክልሉ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የሰብዓዊ ርዳታ ለማቅረብ የሚደረውን ጥረት ማደናቀፉን አክሎ ገልጿል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ግጭቱ አንዲቆም በተቻለው መጠን ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን መጠቀም አለበት ሲል ድምዳሜ ሰጥቷል።

ግጭት ለማስቆም የዩኬ መንግሥት ከተባበሩት መንግሥታት፣ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት፣ በግጭቱ ተሳታፊ ከሆኑ አካላት እና ከጎረቤት አገራት ጋር አብሮ መስራት አለበት ብሏል ፓርላማው።

የዩኬ ፓርላማው ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ ላይ በተለይ በሴቶች እና ሕጻናት ላይ የተቃጣው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች እጅጉን እንዳሳዘነው ገልጾ፤ ወንጀሉ ተመርምሮ ጥፋተኞች ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብሏል።

በትግራይ ክልል የተፈጸሙ ወንጀሎች በገለልተኛ አካል እንዲጣራ እና ጥፋተኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ የዩኬ መንግሥት ትብብር ማድረግ እንዳለበት አሳስቧል።

ዜጎችን ከጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች መጠበቅ የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊነት መሆኑን የብሪታኒያ መንግሥት የኢትዮጵያን መንግሥትን ማሳሰብ አለባት ሲል ፓርላማው ምክረ ሃሳቡን ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎቹን ደህንነት ለማረጋገጥ እርምጃ መውሰድ ቢሳነው፤ የዩኬ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታተ የጄኖሳይድ ኮንቬንሽንን መሠረት ባደረገ መልኩ ኃላፊነት የመውሰድ ግዴታ እንዳለበት ማወቅ አለበት ብሏል ፓርላማው።

የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በትግራይ ክልል የተፈፀሙ ወንጀሎች በአግባቡ ተመርምረው አጥፊዎቹ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንዲሰራ ጠይቋል።

የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች በትግራይ እና በጎረቤት ክልሎች የእለት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አካላት መድረስ እንዲችሉ ያልተገደበ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲችሉ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ ደግሞ ግጭት ቆሞ ሰላማዊ መንገድ እንዲፈለግ ከሚደረገው ከዲፕሎማሲያዊ ጥሪቶች መታገዝ እንዳለበት ጠቁመዋል።

በትግራይ ክልል ያለው ግጭት በቀጠለ ቁጥር በቀጠናው የሚገኙ አገራትን መጉዳቱ እና ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ የገለፀው ሪፖርቱ አክሎም ዩናይትድ ኪንግደም በአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በቀይ ባህር አካባቢ የምታደርገውን የልማት ስራዎች ላይ ጫና ይኖረዋል ብሏል።

ኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ጋር ባላት ሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት እስካሁን ድረስ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል ከፍ ያለ ገንዘብ አለመመደቡ እንዳስደነቃቸው የሕዝብ እንደራሴዎቹ በሪፖርታቸው ላይ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ