የሕዝብን ቆሽት ያሳረረው የሕዳሴው ግድብ መንግስታዊ ዘረፋ ላይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል።

የሕዳሴውን ግድብ ለመገንባት የተዋጣው ገንዘብን አስመልክቶ የተደረገውን መንግስታዊ ዝርፊያ የሰማው ሕዝብ ቆሽቱ አሯል ቢባል ያስኬዳል ፤ ይህ ጉዳይ ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ ለመግለጽ እንደተሞከረው በግንባታው ስም ከፍተኛ ገንዘብ ለብክነት ከመዳረጉም በላይ እስከ ሕይወት መጥፋት ዘልቋል። ሕዳሴ ሲገለጥ በሚል ርዕስ ዋልታ ባዘጋጀው የምርመራ ዘገባ የሕዳሴው ግድብ በሰባት አመት ውስጥ ያለበት አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ከ25 እስከ 30 በመቶ ብቻ መሆኑን ዘግቧል። ይህም በዘረፋው ጥቃት ከደረሰባቸው ክፍሎች አንዱ መሆኑ ግንባታውን መጎተት ብቻ ሳይሆን ገድሎታል።

ሃገርን በተቀነባበረ መልኩ ሲዘርፍ የነበረው የኢሕ አዴግ የሌቦች አንጃ ስለ ሕዝብ እድገትና ስለ ሃገር ልማት ደንታ ቢስ በመሆን በልማት ሽፋን ከፍተኛ ወንጀል ሰርቷል። ይህንን ከፍተኛ የምዝበራ ወንጀል እንዲሁ በይቅርታና በምሕረት ማለፍ በሃገር ላይ ክሕደት ከመፈጸም አይለይም። ምዝበራው በረቀቀ መልኩ መፈጸሙ ብቻ ሳይሆን የኢንጂነር ስመኘውን ሕይወት እስከ መቅጠፍ ከዚያም በላይ ገዳዮቹ እንዳይገኙ ከፍተና አሻጥር በመፈጸም በምርመራው ላይ ተጽእኖ በማሳደር መረጃ በማጥፋት ከፍተኛ ተንኮል በመፈጸም የወንጀሉ አቀናባሪዎችና ፈጻሚዎች ዱካ እንዳይገኝና ምርመራ እንዳይደረግ አቃቢ ሕግ መግለጫውን በተደጋጋሚ እስኪሰርዝ ድረስ ያላቸውን ጉልበት ተተቅመው መንግስትን ዝም እያሰኙት ነው። የሕግ የበላይነት ማረጋገጥ የሚቻለው መንግስታዊ ዘራፊዎችንና ገዳዮችን መቅታት ሲቻል ብቻ ነው።

የኢትዬጲያ ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው ነበር ይህን ግድብ ለአምስት ተከታታይ አመታት ነገር ግን በ5 አመት ይጠናቀቃል የተባለው የህዳሴው ግድብ ግንባታም ቢሆን ከ25ና ከ30 በመቶ በላይ አለመጠናቀቁም ታውቋል።የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትርም እንደተናገሩት የተሰበሰቡት ኮንትራክተሮች እንኳን ግድቡን ሊሰሩት እንደዚህ አይነት ግድብ እንኳ አይተው አያውቁም ማለታቸው አይዘነጋም
በተያያዘም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ባለቤትነት እንዲሁም በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) እና ሳሊኒ ኩባንያ የስራ ተቋራጭ የሆኑበት የሕዳሴው ግድብ አፈጻጸም ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ብክነትና ምዝበራ የተፈጸመበት መሆኑ ተገልፃል

“ሕዳሴ ሲገለጥ” በሚል ርዕስ ዋልታ ኢንፎርሜስን ማዕከል ባዘጋጀው የምርመራ ዘገባ የሕዳሴው ግድብ በሰባት አመት ውስጥ ያለበት አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ከ25 እስከ 30 በመቶ ብቻ መሆኑን አመላክቷል።በተለይም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራውን የተረከበው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) ያለጨረታ ፕሮጀክቱን አጠናቆ ለማስረከብ በ25 ነጥብ 58 ቢሊየን ብር ተዋውሎ ስራውን መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር አብርሃም በላይ ገልጸዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለው እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ እስከ አሁን ድረስ ወደ 16 ነጥብ 79 ቢሊየን ብር ክፍያ ተፍጽሞለታል ይህ ክፍያ ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ክፍያ 65 በመቶ ይሸፍናል። በሌላ በኩል የሜቴክ የስራ አፈጻጸም 42 በመቶ ያህል ብቻ መሆኑን ዶክተር አብርሃም አስታውቀዋል የሕዝብን ቆሽት ያሳረረው የሕዳሴው ግድብ መንግስታዊ ዘረፋ ላይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል። #MinilikSalsawi