ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ እያደረሰ ያለው ጉዳት እና ያሉት ምርጫዎች

ማድረግ የነበረብንን ያለማድረጋችን እየከፈልን ያለነውን ዋጋ የከፋ አድርጎታል። አሁንም ልናደርግ የምንችላቸው ነገሮች መኖራቸው ግን የቀሩንን አማራጮች ለመጠቀም የተስፋው መስኮት ጨርሶ ሳይዘጋ እና ማሰብ እንኳን የሚያዳግተው ሳይከተል መንቀሳቀስ ንግድ ይላል። ከገዛ ራሳችን ስህተቶችም ሆነ ከሌሎች ፈተናዎች የሚቀሰሙ በርካታ ቁምነገሮች አሉ።