ይድረስ ለጀግናው የአማራ ሕዝብና አገር ወዳድ ወገናችን ሁሉ በያላችሁበት

ይድረስ ለጀግናው የአማራ ሕዝብና አገር ወዳድ ወገናችን ሁሉ በያላችሁበት!

ከኢትዮጵያ አገር አድን ግብረሃይል የቀረበ ሃገራዊ ጥሪ

የዛሬ ሦስት ዓመት በሃገራችን ከዳር እስከዳር በተቀጣጠልው ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት የተስፋ ጮራ ፈንጥቆ ነበር። ግን እንደአለመታደል ሆኖ በቡራዩ ወገኖቻችን ሲታረዱ፣ በለገጣፎ በኦነጋውያን የኗሪዎች ቤት በላያቸው ላይ ሲፈርስ ተስፋችን በለጋነቱ ከሰመ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ለአፍሪካ ሕዝብ የነፃነት ተምሳሌት የሆነችው ሃገራችን በአገር በታታኝ ሃይሎች ሴራ ለመፈረካከስ በመንደርደር ላይ ትገኛለች።

የቀድሞው ሕወሃት መራሹ አገዛዝ፣ በሕዝቡ ላይ ባሳደረው መከራ፣ ግፍ፣ ጭቆና፣ የንብረት ዘረፋና የዘር ፍጅት የተነሳ በቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ፣ የሕወሃት ባለሥልጣኖችን ከመንበራቸው ፈንግሎ፣ በቦታው የተሰየመው የዛሬው የብልፅግና ጥምረት ለኢትዮጵያን አንድነት፣ የሕዝቡ ሰላም፣ አብሮነትና እኩልነት ፀር የሆነውን በልዩነት ላይ የተመሠረተ የመንግሥት አደረጃጀትና አማራን በጠላትነት ፈርጆ የተዘጋጀውንና  የዚሁ ማስፈጸሚያ የሆነውን ሕገ-መንግሥት ለማሻሻል ወይም ለመቀየር ፍላጎት ባለማሳየቱ የአገሪቱና የሕዝቡ ችግር ከድጡ ወደ ማጡ ተሸጋግሯል። በዚህም የተነሳ አዲሶቹ የሥልጣን ተረኞች፣ ባለፉት 60 ዓመታት “አማራ ቅኝ ግዛት አድርጎ ይዞናል፤ ባህላችንን፣ ቋንቋችንን ማንነታችንን አጥፍቶብናል” እያሉ በዓለም አደባባዮች ሲያሰሙት የነበረውን ባዶ ጩኸት፣ ወደመሬት በማውረድ፣ አማራውን በወለጋ፣ በአርሲ፣ በሐረርጌ፣ በባሌ፣ በኢሉ ባቡር፣ በአዲስ አበባ፣ በዝዋይ፣ በአዳሚቱሉ፣ በሻሻመኔ፣ በአጋርፋ፣ በመተከል፣ በአሶሳ፣ ወዘተ በግፍ በጅምላ የመንግሥትን መዋቅር ተጠቅመው እንዲገደል ከማድረጋቸውም በላይ፣ እንዲፈናቀል እያደረጉት ነው።

የአሁኑን አገዛዝ ከወያኔ የሚለየው አማራው ከጎንደር ክፍለሀገርም ሳይቀር እንዲፈናቀል ማድረጉ ነው። ከመተከልና ከአዲስ አበባም እንዲለቅ ማስገደዱ ነው። በግልጽ አዲስ አበባ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መንግሥት ሽመልስ አብዲሣ አማራው ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን በተገኘበት “ነፍጠኞች በሰበሩን ቦታ ሰበርናቸው!” ብሎ መፎከሩ ብቻ ሳይሆን፣ በአንድ የሚስጥር ስብሰባ “አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፣ ይህም እውን እንዲሆን፣ አብዛኞቹን አሳምነን፣ በቀሩት ላይ ውዥንብር ፈጥረን ኢትዮጵያ ኦሮሞን እንድትመስል እናደርጋለን፤ ወያኔ ለዓላማው ማስፈጸሚያ ኢሕአዴግን እንዳደራጀ ሁሉ፣ እኛም ብልጽግናን ያደራጀነው ኦሮሙማን እውን ለማድረግ በመሣሪያነት እንዲያገለግለን ነው” ማለቱ ነው። ከዚህ እሳቤ ስንነሳ ፣ ብልጽግና በተለይም የኦሮሞ ብልፅግና የለየለት የአማራ ጠላት አይደለም ማለት አይቻልም።

የአሁኑ ብልፅግና የትናንቱ ወያኔ/ኢሕአዴግ ሌላው ገፅ ነው። የጠገበውን ጅብ አባሮ፣ የተራበውን ጅብ በኢትዮጵያ ላይ ያሠማራ፣ የይሉኝታ ወሰን የማይገድበው፣ በሕዝባችን ላይ የተጫነ ‘ሁሉም የኔ ነው’ የሚል ስግግብ ቡድን ነው። በመሆኑም ባለፉት ሦስት ዓመታት በአማራው ላይ የከፋና የሚዘገንን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲፈጸምበት አድርጓል ወይም በዝምታ ተመልክቷል። ይህ እንዲቀጥል አማራውም ሆነ ሌሎች ሰላምና አንድነት አፍቃሪ የሆኑ ሁሉ ሊፈቅዱለት አይገባም። ዛሬም እንደትናንቱ እምቢ! አሻፈረኝ ልንል ግድ ይለናል።

ጀግናው የአማራ ሕዝብ ሆይ! ጠላቶችህ እንደ አሸዋ የበዙ፣ እንደሠርዶ የተታቱ ናቸው። ጠላቶችህ የበዙት፣ አንተ በድለሃቸው ሳይሆን፤ ለአብሮነት፣ ለኢትዮጵያዊነት፣ ለመቻቻልና ለነፃነት ቀናዒ በመሆንህ፣ ይህን ደግሞ የኢትዮጵያዊነት የውስጥና የውጭ ጠላቶች ስለማይፈልጉት ነው። በጥቅሉ በደልና ውርደትን አልቀበልም በማለት፣ ተዋራጅና ተሰዳጅ ሊያደርጉህ በየቀኑ እንደ ሐምሌ ጐመን ይቀረድዱሃል። የተላበስካቸው ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ አስተዳደራዊ፣ ወዘተ እሴቶችህ፣ ነፃነት ወዳድ እና አልደፈርም ባይነትህ የውስጥና የውጭ ጠላት እንድታፈራ አድርገውሃል። አማራነትህ ከኢትዮጵያዊነት ጋር ተለንቅጦ የተደቆሰ መሆኑ፣ ይህ እጥፍ ድርብ ማንነትህ ጠላቶችህ እንዲበዙ አድርጓቸዋል። ዛሬ ከዚህ እጥፍ ድርብ ማንነትህ ለመነጠል፣ ጠላቶችህ እንቅልፍ አጥተው እየሠሩ ነው። የሚያጠቁህ፣ ስለሚፈሩህ ነው። የሚያጠቁህም ጥቃትን የማትሸከም፣ ውርደትን የማትቀበል፣ ነፃነት ወዳድ በመሆንህ ነው። ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ዳብሮ መቀጠል እርሾው አንተ መሆንክን ስለሚያውቁ ነው። የኢትዮጵያ ጠላቶች፣ ኢትዮጵያን በፈለጓት መልክ በእጃቸው መዳፍ ውስጥ የሚያስገቧት አንተ(አማራ) ስትዳከም፣ ስትከፋፈል፣ ተስፋ ስትቆርጥ፣ የዚህ ሁሉ ድምር ተሸናፊ ስትሆን እንደሆነ በሚገባ ስለሚያውቁ፣ ባንተ ላይ ከፕሮፓጋንዳ እስከ አካላዊ ጦርነት የደረሰ ጥቃት እየፈፀሙብህ ነው።  ጥቃቱ ግን ይበልጥ ያጠነክርሃል እንጂ፣ አያላላህም፣ አያዳክምህም። ስለሆነም ጀግናው የአማራ ሕዝብ ሆይ “ጅብ ከሚበላህ፣ ጅብ በልተህ የምትቀደስበት” ወቅት ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው!!!

“ባርነቱን ያወቀ ባሪያ ግማሽ ነፃ ነው!”  እንደሚባለው፣ አማራው ለህልውናው ተጠብቆ መዝለቅ በቁርጠኝነት የሚተጋ የተደራጀ የፖለቲካ ድርጅት፣ የክልል ወይም የፌዴራል መንግሥት የሌለው መሆኑን ማወቅና አምኖ መቀበል፣ አማራው ህልውናውን ለማስጠበቅ ለሚያደርገው ትግል የመጀመሪያው የማንነቱ መሠረት ነው። በዛሬዋ ኢትዮጵያ በስም ካልሆነ በስተቀር አማራው ካለራሱ ቁርጠኝነት በስተቀር ሌላ ጠበቃና አለኝታ የለውም። ወደድንም ጠላንም ብአዴን/አዴፓ አሁን የአማራ ብልጽግና የሚባሉት የዳቦ ስሞች፣ ለአማራው መቁረጫና መፍለጫ በምሣር እጀታነት የተደራጀ ቀደም ሲል የትሕነግ ዛሬ ደግሞ የኦሮሞ ብልፅግና ዓላማ ማስፈጸሚያ መሣሪያ ነው። ዛሬ አማራው ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የሚፈጸምበት መንግሥታዊ መዋቅሩን በተቆጣጠሩ ፀረ-አማራ ቡድኖች ነው። በዚህ ውስጥ ብአዴን/አዴፓ/የአማራ ብልፅግና የለም ለማለት አይቻልም። የሆነው ሆኖ አማራው ከሚደርስበት የተቀናጀ ጥቃት ራሱን ለመታደግና ሃገራችንን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍ ከሌሎቹ አገር ወዳድ ወገኖቹ ጋር መሥራት ግድ ይለዋል።

በተለያዩት የሃገራችን ክፍል የምትገኙ ወገኖቻችን ሆይ! ዛሬ በአማራው ላይ የተከፈተው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ነገ በናንተም ላይ የሚከሰት መሆኑን እንደምትገነዘቡ እርግጠኞች ነን። በተረኞቹ በተዛባ የስግብግብነት አካሄድ በማንነታችሁ በየጊዜው ሰለባም እንደምትሆኑ የተመዘገበ ነው። ቢሆንም በአማራው ወገናችሁ ላይ በስፋት እየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት ዛሬ በናንተ ላይ ባይደርስም ነገ ግን ተራችሁ እንደሚሆን ይጠፋችኋል ብለን አንገምትም። በቁጥራችሁ አናሳ የሆናችሁትን ወገኖቻችንን በተለያየ መንገድ በማስፈራራት ከቀያችሁ ስትፈናቀሉ አላያም ስትገደሉ እያየን ነው። በአማራው ሕዝብ ላይ የተጋረጠው የህልውና ጥያቄ በናንተም ላይ እያንዣበበ መሆኑ የማይካድ ነው። ስለዚህ የኛ የሕዝቦቿ ህልውና ከውድ ሃገራችን ከኢትዮጵያ ህልውና ጋር የተያያዘ ስለሆነ ስግብግብነትና ተረኝነትን በጋራ መቋቋም ግድ ይለናል። ኢትዮጵያን በጋራ ይዘናት እንድንዘልቅ ታሪካዊ አደራ በሁላችንም ላይ ወድቋል። በአንድነት በመቆም ይህንን ካላደረግን ሰሞኑን በአማራ ክልል በኦሮሞ ልዩ ዞን የተፈጸመውን የሚመስል ወረራ የእናንተም እጣ ፋንታ በናንተም ላይ እንደሚፈፀም በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። የአንዳንድ ጥንፈኛ ብሔርተኞች በእስር ላይ መሆንና ፍርድ ቤት መመላለስ ሊያዘናጋችሁ አይገባም። ታሰሩም አልታሰሩም፣ ተፈረደባቸውም አልተፈረደባቸውም ዛሬ በስራ ላይ ሲውል የምናየው ከነሱ የተሻለ ሃሳብ አይደለም። እንደቅርብ ጊዜ ምሳሌ የ125ኛ የአድዋ ድል በዓል ሲከበር ተረኞች ጦርነቱን የመሩትን አፄ ምኒልክን እንዴት እንዳዋረዷቸው ማስታወስ ይበቃል። ስለዚህ አገራችንን በጋራ እንድናድናት ለአማራውና ለሌላውም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በያላችሁበት ክልል ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።

የአማራው ህልውና በልጆቹ ተገቢ መስዋዕትነት ይረጋገጣል!

የኢትዮጵያ አንድነት በሃገር ወዳዶች መስዋዕትነት ይጠበቃል!

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ አገር አድን ግብረሃይል
ኤፕሪል 15, 2021