በየምርጫ ጣቢያዎቹ መዝጋቢም ተመዝጋቢም የለም

ኢትዮጵያ ዉስጥ በመጪዉ ግንቦት ማብቂያ በሚደረገዉ ምርጫ ድምፅ የሚሰጡ መራጮች መመዝገብ ከጀመሩ ሁለት ሳምንት ደፈነ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣዉ የጊዜ ሰለዳ መሠረት በየአካባቢዉ የመራጮች መመዝገቢያ ማዕከላት መዘጋጀታቸዉም እየተነገረ ነዉ። በአማራ ክልላዊ መስተዳድር ርዕሠ ከተማ በባሕርዳር ከተማ የተዘጋጁት የመመዝገቢያ ሥፍራዎች ግን እስከ ዛሬ ድረስ መዝጋቢም፣ ተመዝጋቢም የለባቸዉም። የባሕርዳሩ DW ወኪላችን ያነጋገራቸዉ የከተማይቱ ነዋሪዎች እንደሚሉት በየመዝገቢያ ጣቢያዉ ሔደዉ መዝጊቢ አላገኙም። ምርጫ ቦርድ ግን ባሕር ዳር ዉስጥ ከሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በ80 ከመቶ ምዝገባ ተጀምሯል ባይ ነዉ። DW