የውጫዊ ጫናና የአገር ውስጥ ቀውስ አገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ እንደጣላት ምሁራን አመለከቱ።

ለኢትዮጵያ መንግስት ምሁራን ያደረጉት ጥሪ

የውጫዊ ጫናና የአገር ውስጥ ቀውስ አገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ እንደጣላት ምሁራን አመለከቱ፣ አገሪቱን ከመፈራረስ ለማዳን የውስጥ ችግሮቻችንን መፍታት ለነገ የማይሰጥ የቤት ስራ እንደሆነ ነው ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ምሁራን ያመለከቱት። ምሁራኑ ገዥው ብልፅግና ፓርቲ «ተዋህጃለሁ» ቢልም በተግባር ከብሔርና ከክልል አጥር አልወጣም ብለዋል። አህአዴግ የሚባለው ፓርቲ ፈርሶ ሌሎች አጋር ድርጅቶችን አካትቶ ብልፅግና የተባለው ገዥው ፓርቲ ቢመሰረትም የተግባር አንድነት የሌለው በመሆኑ አሁንም ከብሔርና ከክልል አጥር ባለመውጣቱ ልዩነቶች እየሰፉ የዜጎች መጎሳቆል መቀጠሉን አመልክተዋል። አሁን እየታየው ያለው የውጪ ጫናና የውስጥ ሽኩቻ አገሪቱን ከመበበታተኑ በፊት ኢትዮጵያውያን በአስተውሎት መራመድ እንደሚገባቸው ምክራቸውን ለግሰዋል። DW